የእግርኳስ ፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ

በግንቦት ወር 2010 አፋር ላይ በተደረገው ምርጫ የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል በመሆን የተመረጡት ግለሰብ በፖሊሰ ቁጥጥር ስር ውለዋል።

የጋምቤላ ክልልን በመወከል በፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት እና በአሁኑ ወቅት የፀጥታ ክፍል ኃላፊ በመሆን ተመድበው እያገለገሉ የሚገኙት አቶ ቻን ጋትኮች ትላንት ከአዲስ አበባ በአንድ አካባቢ በገንዘብ ብክነት ተጠርጥረው በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል።

አቶ ቻን ጉዳያቸው በጋምቤላ ፍርድ ቤት የሚታይ ሲሆን በቀጣይ የሚኖረውን የፍርድ ውሳኔ ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ
በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡