የደደቢት ተጫዋቾች ወደ ልምምድ ተመለሱ

ላለፉት ሦስት ቀናት ልምምድ አቁመው የነበሩት የሰማያዊዎቹ ተጫዋቾች ዛሬ ወደ ልምምድ ተመልሰዋል።

በደሞዝ አለመከፈል ምክንያት ላለፉት ቀናት ልምምድ አቁመው የነበሩት የደደቢት ተጫዋቾች ከነገው ጨዋታ አስቀድሞ ዛሬ ጠዋት ወደ መደበኛ ልምምዳቸው መመለሳቸው ታውቋል። ሆኖም ተጫዋቾቹ ወደ ልምምድ የተመለሱት በምን ቅድመ ሁኔታ እንደሆነ ለማወቅ ባይቻልም ከዋና አሰልጣኙ እና ከቡድኑ አመራሮች ባደረጓቸው ንግግሮች ወደ ልምምድ ሊመለሱ እንደቻሉ ይገመታል።

በቡድኑ ከጋናዊው አጥቂ ኑሁ ፉሴይኒ ውጪ ሁሉም ተጫዋቾች ለነገው ጨዋታ ዝግጁ መሆናቸው ሲታወቅ በሁለተኛው ዙር በጉዳት ምክንያት ቡድናቸው ማገልገል ያልቻሉት አቤል እንዳለ እና ኩማ ደምሴ ከጉዳት መልስ ጅማን ከሚገጥመው ስብስብ ውስጥ ይቀላቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በተያያዘ ዜና የጅማ አባ ጅፋር የቡድን አባላት ጨዋታው እንደሚካሄድ እርግጥ ከሆነ በኋላ ተከፋፍለው ወደ መቐለ እየተጓዙ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡