ከፍተኛ ሊግ፡ ደ/ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፈርሶ ሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን ተተክቷል

 

ዘንድሮ የተመሰረተውና ከፕሪሚየር ሊጉ ቀጥሎ የሚገኘው ሊግ የሆነው ከፍተኛ ሊግ በቅርቡ እንደሚጀመር ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡ ክለቦችን መመዝገብ መጀመሩም ታውቋል፡፡

ፌዴሬሽኑ እንዳስታወቀው አምና ለብሄራዊ ሊግ ማጠቃለያ ውድድር ደርሶ ከምድቡ የተሰናበተው ደብረማርቆስ ከነማ ፈርሷል፡፡ በከፍተኛ ሊግ ከሚካፈሉ 32 ቡድኖች አንዱ የነበረው ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ለመፍረሱ ከዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ይፋዊ የሆነ ምክንያት እስካሁን ባይቀርብም በበጀት እጥረት ምክንያት ቡድኑን ለመበተን መገደዱን ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲን መፍረስ ተከትሎ ሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን ከነማ ወደ ከፍተኛው ሊግ የማደግ እድል አግኝቷል፡፡

ከከፍተኛው ሊግ ክለብ ሲፈርስ ይህ ለ2ኛ ጊዜ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም በአምናው የብሄራዊ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር ላይ ከደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ጋር በአንድ ምድብ ውስጥ የነበረው ሼር ኢትዮጵያ መፍረሱ የሚታወስ ነው፡፡

ለማስታወስ ያህል በከፍተኛው ሊግ የሚካፈሉት ክለቦች እነዚህ ናቸው፡-

[table id=38 /]

ማስታወሻ – ሱፐር ሊግ ይህ ውድድር በተለምዶ የሚጠራበት ስም ሲሆን ፌዴሬሽኑ ለውድድሩ የሰጠው ይፋዊ ስያሜ ከፍተኛ ሊግ የሚል ነው፡፡

-ከላይ የሚታየው ምስል የፈረሰው የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ክለብ ነው፡፡

ያጋሩ