ጅማ አባጅፋሮች ከኢትዮጵያ ዋንጫ ራሳቸውን ሊያገሉ ይችላሉ


በኢትዮጵያ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ በመጪው ረቡዕ ከወላይታ ድቻ ጋር በሶዶ ስቴድየም እንደሚጫወቱ መርሀ ግብር መውጣቱ የሚታወቅ ነው። ሆኖም ጅማዎች ወደ ውድድሩ ስፍራ የማምራታቸው ነገር አጠራጥሯል።

ጅማዎች ከመቐሌው ጨዋታ በኋላ ዛሬ መስራት የነበረባቸውን ልምምድ እንዳርሰሩ ታውቋል። ልምምድ ለማቆማቸው እንደምክንያት የተጠቀሰውም ከደምወዝ ጥያቄ ጋር የተያያዘ መሆኑ ለማወቅ የተቻለ ሲሆን ለረቡዕ ጨዋታ ወደ ሶዶ መጓዝ የነበረባቸው ቢሆንም እስከ ዛሬ አመሻሽ ድረስ ወደ ስፍራው አላቀኑም። ይህም ከጨዋታው ራሳቸውን ሊያገሉ እደሚችሉ ያመላክታል።

ሶከር ኢትዮጵያ ባገኘችው ተጨማሪ መረጃ መሠረት ክለቡ ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከጨዋታው ራሱን ማግለሉን የሚገልፅ ደብዳቤ መላኩ የተገለፀ ሲሆን በጉዳዩ ዙርያ የክለቡን አመራሮች በስልክ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ባለመሳካቱ የክለቡን አመራሮች ሀሳብ ማካተት አልተቻለም፡፡

በተሳታፊዎች ራሳቸውን ማግለል ምክንያት አልሞላለት ባለው የኢትዮጵያ ዋንጫ ደደቢት እና ስሑል ሽረ ራሳቸውን ማግለላቸው የሚታወስ ሲሆን አምና ደደቢት፣ ኤሌክትሪክ እና ጅማ አባጅፋርም ተመሳሳዩን አድርገው እንደነበር ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡