ሲያወዛግብ ያደረው የሊግ ኮሚቴ ውሳኔ ማሻሻያ ሊደረግበት ነው

በ26ኛው ሳምንት ወላይታ ድቻ ከ ፋሲል ከነማ ያደረጉትን ጨዋታ ተከትሎ ፋሲል ከነማ የተጫዋች ተገቢነት ክስ ማስያዙ ይታወቃል። 

የፌዴሬሽኑ ሊግ ኮሚቴ ትላንት ማምሻውን ባደረገው ስብሰባ ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ ወላይታ ድቻ በ15ኛው ሳምንት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ባደረገው ጨዋታ ላይ በረከት ወልዴን በአምስት ቢጫ ማሳረፍ ሲገባው አላሳረፈም በማለት የፋሲል ከነማን ቅሬታ ተቀብሎ ውሳኔውን ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሦስት ነጥብ እና ሦስት ንፁህ ጎል ማምሻውን በወጣ ደብዳቤ ፎርፌ መስጠቱ ይታወሳል።

አሁን እንዳገኘነው መረጃ ደግሞ ወላይታ ድቻ ተጫዋች በረከት ወልዴን በተስተካካይ ጨዋታ ከሲዳማ ቡና ጋር ባደረጉት ጨዋታ ማሳረፉን ቅሬታውን ለፌዴሬሽኑ አቅርቧል። የሊግ ኮሚቴም በድጋሚ ዛሬ ጠዋት አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ ሳይመረምር ቀርቶ የወሰነውን ውሳኔ እንደገና ማሻሻያ በማድረግ አስቀድሞ የወሰነው ውሳኔ ውድቅ (ስህተት) መሆኑን የሚገልፅ ደብዳቤ እንደሚያወጣ ሰምተናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡