ዋሊድ አታ ከጊልሰንቢሪሊጊ ጋር ተለያየ

 

ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ተከላካይ ከቱርኩ ጊልሰንቢሪሊጊ ጋር በይፋ ተለያይቷል፡፡

ዋሊድ በኤፕሪል 2015 የስዊድኑ ቢኬ ሀከንን ለቆ የአንካራውን ክለብ በ3 አመት ኮንትራት ከተቀላቀለ ወዲህ የተሳካ ጊዜ ማሳለፍ አልቻለም፡፡

በውድድር ዘመኑ 4 ጨዋታ ብቻ ያደረገው ዋሊድ ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለፀው ከክለቡ ጋር በስምምነት ተለያይቷል፡፡

ዋሊድ በዚህ ሳምንት ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ባደረገው ቆይታ በክለቡ በቂ የመሰለፍ እድል ባለማግኘቱ ክለቡን መልቀቅ እንደሚፈልግ መናገሩ የሚታወስ ነው፡፡

በቱርክ ሊግ 16ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ጊልሰንቢሪሊጊ በዚህ ሳምንት አሰልጣኙን ማሰናበቱን ተከትሎ የአለም የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ስቧል፡፡ ክለቡ በ2015 ብቻ 5 አሰልጣኞች ቀይሯል፡፡

ያጋሩ