ወላይታ ድቻ በፎርፌ 3 ነጥብ አግኝቷል

በ27ኛው ሳምንት ከተያዙት የኢትዮጽያ ፕሪምየር ሊግ መርሃግብሮች ውስጥ ሶዶ ላይ ሊካሄድ የነበረው የወላይታ ድቻ እና ጅማ አባጅፋር ጨዋታ ጅማዎች ባለመገኘታቸው በደንቡ መሠረት የፎርፌ ውሳኔ ተግባራዊ ሆኗል።

ጅማ አባጅፋሮች ከተጫዋች የደሞዝ ክፍያ ጋር በተያያዝ በገጠማቸው ችግር ምክንያት ያሳለፍነውን ሳምንት የቡድኑ ስብስብ ምንም ዓይነት ልምምድ ያላደረጉ ከመሆኑ ጋር ወደ ሶዶ ሳያመሩ ቀርተዋል። በመሆኑም የዕለቱን መርሀግብር የሚዳኙት ዳኞች በህጉ መሠረት ድቻዎች በሜዳ ላይ 30 ደቂቃዎችን እንዲያሳልፉ በማድረግ የእለቱን ጨዋታ ፎርፌ በመስጠት አጠናቀዋል።

በዚህም መሰረት በሊጉ ለሁለተኛ ጊዜ። ፎርፌ (3 ነጥብ እና 3 ጎል) ያገኘው ወላይታ ድቻ ነጥቡን 34 በማድረስ በወራጅ ቀጠና ከሚፎካከሩ ቡድኖች የተሻለ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

ወላይታ ድቻ በዛሬው ጨዋታ ባሳለፋነው ሳምንት የሊጉ መሪ ፋሲል ከነማን ከረቱበት ስብስብ እሸቱ መናን በ5 ቢጫ ካርድ አሳርፎ በምትኩ ሳምንት የድል ግቧን ያስቆጠረውን ኃይሌ እሸቱን በመጠቀም ነበር ወደ ሜዳ ሊገቡ የነበረው።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡