የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ ሊደገም ነው

ባለፈው ሳምንት በአወዛጋቢ የዳኝነት ውሳኔ ምክንያት ተቋርጦ በኤስፔራንስ ቻምፒዮንነት ተጠናቆ የነበረው የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ሊደገም ነው።

በአፍሪካ እግርኳስ ዙርያ የሚዘግቡ በርከት ያሉ ጋዜጠኞች የካፍ ኮሚቴ አባላትን በምንጭነት ጠቅሰው እንደዘገቡት ከሆነ ኮሚቴው ኤስፔራንስ ደ ቱኒዝ ዋንጫውን ያነሳበት መንገድ ተገቢ ነው አይደለም የሚለው ጉዳይ በጥልቀት አይቶ የፍፃሜ ጨዋታው እንዲደገም እና ጨዋታውም ከአፍሪካ ዋንጫ በኃላ እንዲካሄድ መወሰናቸው ገልፀዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ የካፍ ፅህፈት ቤት በይፋ ያለው ነገር ባይኖርም ኤስፔራንሶች ሜዳልያቸውን እና ሞላላውን ዋንጫ መመለሳቸው እንደማይቀር በርካቶች እየተናገሩ ይገኛሉ።

ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ቫር በአግባቡ መጠቀም ያልሆነለት ካፍ ባለፈው ዓመትም በተመሳሳይ የፍፃሜ ጨዋታ መሐል የቫር ቴክኖሎጂ አቁሞ ኢትዮጵያዊው የመሃል ዳኛ ባምላክ ተሰማ በግል ጥረቱ ጨዋታው እንከን አልባ ሆኖ በሠላም እንዲጠናቀቅ ማድረጉ ይታወሳል።

ካስፈለግዎየቻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ድራማ


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡