ፌዴሬሽኑ ድሬዳዋ ከተማ ባሰናበታቸው ተጫዋቾች ጉዳይ ላይ ውሳኔን ሰጥቷል


ድሬዳዋ ከተማ በሁለተኛው ዙር ጅማሮ ላይ ከክለቡ ያሰናበታቸው ኃይሌ እሸቱ፣ ዮናታን ከበደ እና ወሰኑ ማዜን በተመለከተ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ውሳኔ አስተላልፏል።

ሦስቱ ተጫዋቾች “ከክለቡ ውል እያለብን ያለ አግባብ ተሰናብተናል።” በማለት ክስ ማቅረባቸው የሚታወስ ሲሆን ፌድሬሽኑ ጉዳዩን ሲመለከት ከቆየ በኃላ ለዮናታን ከበደ እና ወሰኑ ማዜ እና አሁን በወላይታ ድቻ ለሚገኘው ኃይሌ እሸቱ ደሞዛቸውን በ10 ቀን ውስጥ እንዲከፍላቸው ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

የውሳኔው ደብዳቤ ይህን ይመስላል


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡