ለኢጋድ ከ18 አመት በታች ሴቶች ዋንጫ ወደ ጅቡቲ የሚያቀኑ 20 ተጫዋቾች ይፋ ሆኑ

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን እድሜያቸው ከ18 አመት በታች በሆኑ ሀገራት መካከል በሚደረገው የኢጋድ (የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት) አባል ሃገራት ውድድር ላይ ይካፈላል፡፡ 

በንግድ ባንኩ አሰልጣኝ አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የሚመራው ከ18 አመት በታች ሴቶች ቡድን ባለፈው ሳምንት 24 ተጫዋቾች ተመርጠው ዝግጅት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

አሰልጣኝ ብርሃኑ ዛሬ ወደ ጅቡቲ የሚያቀኑ 20 ተጫዋቾችን እና 5 ተጠባባቂዎችን ይፋ አድርገዋል፡፡

 

የተመረጡ ተጫዋቾች ዝርዝር

ግብ ጠባቂዎች

ትዕግስት አበራ – ሀዋሳ ከነማ

አክሱማዊት ገ/ሚካኤል – ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ

 

ተከላካዮች

ዘለቃ አሰፋ – ደደቢት

አበዛሽ ሞጌሶ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

ጥሩወርቅ ወዳጄ – ዳሽን ቢራ

ሰናይት በዳሳ – ቅድስት ማርያም

ሰላም ላእከ – ሙገር ሲሚንቶ

ፅጌ አሳምነው – ኢትዮጵያ ቡና

ቤተልሄም ከፍያለው – ኤሌክትሪክ

 

አማካዮች

ኪፊያ አብዱልራህማን – ደደቢት

ፅዮን ፈየራ – ኤሌክትሪክ

ዘይነባ ሰኢድ – ኤሌክትሪክ

ትሁን አየለ – ሲዳማ ቡና

ድንቅነሽ በቀለ – ድሬዳዋ ከነማ

ሶፋኒት ተፈራ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

 

አጥቂዎች

አስራት አለሙ – ሲዳማ ቡና

ቤተልሄም ሰማን – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

አለምነሽ ገረመው – ኤሌክትሪክ

ጽዮን ዋቅጅራ – ሀዋሳ ከነማ

እማዋይሽ ይመር – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

 

በተጠባባቂነት የተያዙ

እየሩሳሌም ሎራቶ – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ፅዮን አበራ – ዳሽን ቢራ

ነጻነት ደርቤ – ዳሽን ቢራ

መሪማ ፈትኡ – ቅድስት ማርያም

ቁምነገር ካሳ – ኢትዮጵያ ቡና

ከ18 አመት በታች ቡድኑ ዛሬ ረፋድ ከ 17 አመት በታች ሴቶች ቡድን ባደረገው ጨዋታ 3-1 አሸንፏል፡፡

የኢጋድ ከ18 አመት በታች ውድድር ጥር 8 የሚጀምር ሲሆን የኢትዮጵያ ልኡካን ቡድን ከ3 ቀን በፊት ወደ አስተናጋጇ ጅቡቲ ያቀናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ያጋሩ