የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ በያዝነው ወር አጋማሽ በግብፅ አስተናጋጅነት 24 ሀገራትን ለመጀመሪያ ጊዜ በማሳተፍ ይጀምራል፡፡ በዚህ ውድድር ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ባይሳተፍም አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱም በቴክኒክ ጥናት ቡድኑ ውስጥ ተካተዋል።
አስራ አምስት አባላት ያሉት ይህ ቡድን ውስጥ የካፍ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱን ጨምሮ ከዚህ ቀደም በአፍሪካ ዋንጫ የደመቁት እንደ ካሊሉ ፋዲጋ፣ ዲያሜንሲ ካማራ እና ዳንኤል አሞካቺ የተካተቱበት ሲሆን በውድድሩ ላይ የሚታዩ ቴክኒካዊ ጉዳዮችን በመታዘብ ሪፖርት ማቅረብ እና የጨዋታ እና የውድድሩ ኮከቦችን መምረጥ የቡድኑ ዋንኛ ተግባር ነው።
ከአሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ በተጨማሪ በዳኝነት የተመረጡት በዓምላክ ተሰማ እና ተመስገን ሳሙኤል ወደ አፍሪካ ዋንጫው የሚያመሩ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ናቸው።
© ሶከር ኢትዮጵያ
በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡