በ26ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በጅማ አባ ጅፋር እና በመቐለ 70 እንደርታ መካከል በጅማ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ላይ የስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰት ተከስቷል ያለው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ቅጣት አስተላልፏል።
በዚህም መሠረት ጅማ አባ ጅፋር ሁለት ጨዋታዎችን ከሜዳቸው ዉጪ በ200 ኪሜ. ርቀት በሚገኝ እና በፌዴሬሽኑ በተመዘገበ ሜዳ ላይ እንዲጫወት፣ በጨዋታው የተፈነከተው የሥዩም ተስፋዬን የህክምና ወጪ እንዲሸፍን እና የ100,000 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ተላልፏል። በመቐለ 70 እደርታ በኩል ደግሞ የቡድን መሪው ከጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የዕለቱን ዳኞች አፀያፊ ስድብ መሳደባቸው በመረጋገጡ የ5000 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣትና የስድስት ጨዋታ እገዳ ተላልፎባቸዋል፡፡
የቅጣት ውሳኔው ዝርዝር ይህንን ይመስላል:-
© ሶከር ኢትዮጵያ
በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡