በታሪክ የመጀመርያ የሆነው የኢትዮጵያ ከ13 ዓመት በታች ታዳጊ ብሔራዊ ቡድን ወደ ቻይና ለሚያደርገው ጉዞ ዝግጅቱን ቀጥሏል።
ከሰኔ 16 – 23 በቻይና ሀገር ሉዲ ከተማ የሀገራቱን ወዳጅነት ለማቀራረብ በማሰብ በአራት የአፍሪካ ሀገራት (ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ታንዛኒያ እና ናይጄሪያ) እንዲሁም ከቻይና ከተለያዩ ግዛቶች በተወጣጡ አራት ቡድኖች፤ በድምሩ በስምንት ቡድኖች መካከል የሚካሄደውን ውድድር ለመካፈል የኢትዮጵያ ከ13 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዝግጅቱን እያደረገ ይገኛል።
ታዳጊ ብሔራዊ ቡድኑ በአሰልጣኝ ኤርምያስ ዱባለ እየተመራ ከሳምንት በፊት የተጫዋች ምርጫ አጠናቆ የመጨረሻ 22 ተጫዋቾችን በመያዝ በአዲስ አበባ ስታዲየም ዝግጅት እያደረገ ሲሆን በነገው ዕለት 3:00 በአዲስ አበባ ስታዲየም የወዳጅነት ጨዋታ እንደሚያደርጉ ሰምተናል። የፊታችን ዓርብ ሰኔ 14 የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው የልዑካን ቡድኑን እየመሩ ወደ ቻይና የሚጓዙም ይሆናል።
የታዳጊ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች የስም ዝርዝር
ግብ ጠባቂዎች: አቤል ዓባይ፣ ዳዊት ዱግማ፣ ኪሩቤል አሰፋ
ተከላካዮች፡ አቤል ንቃሸዋ፣ ዳግም ከበደ፣ በፀሎት መለሰ፣ ከበደ መኮንን፣ ሳሙኤል ተስፋዬ
አማካዮች፡ ረመዳን ሁሴን፣ ኑኢና ሄሪ፣ ቅዱስ ንጉሴ፣ ያፌት ሄኖክ፣ አቤል አብርሃም፣ ፍቃዱ ክንዴ
ዮናታን ሃይማኖት፣ ቴዎድሮስ አድማሱ፣ ዳግም አያሌው
አጥቂዎች፡ ተወዳጅ አስፋው፣ ያብስራ ገረመው፣ ፍፁም ልቅናው፣ እስራኤል ሰለሞን፣ እስጢፋኖስ ጥላሁን
© ሶከር ኢትዮጵያ
በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡