የደደቢት ቡድን መሪ በተላለፈባቸው ቅጣት ዙርያ ቅሬታቸውን ገለፁ

በሃያ አራተኛው ሳምንት ደደቢት በበጀት ምክንያት ወደ ሶዶ ባለማምራቱ ፌደሬሽኑ ደደቢት እና ቡድን መሪው ኤፍሬም አበራን መቅጣቱን ይታወሳል። የቡድን መሪው መቀጣቱ ተገቢ እንዳልሆነ እና ይግባኝ ለመጠየቅ ዝግጅት ላይ እንዳለ ገልፀዋል።

በጉዳዩ ላይ ከሶከር ኢትዮጵያ አጭር ቆይታ ያደረገው ኤፍሬም አንድ ቡድን በበጀት ምክንያት ከውድድሩ ማግለሉን ገልጾ ካበቃ በኃላ ጉዳዩ የማይመለከተው ግለሰብ ለይቶ መቅጣት ሚዛናዊ እንዳልሆነ ገልጿል። ” ጉዳዩ ከኔ ኃላፊነት በላይ ሆኖ እያለ በዚ ጉዳይ እኔ መቅጣቴ በጣም ገርሞኛል፤ ቡድኑ የበጀት ችግር እንዳለበት እየታወቀ ከሌላው የቡድኑ አባል ለይተው እኔን መቅጣት ተገቢ አይደለም። ጉዳዩ የሚመለከታቸው በርካታ ሰዎች እያሉ ቡድን መሪው ተለይቶ የሚቀጣበት ህግ በምን አግባብ ነው የወጣው” ብለዋል።

በፌደሬሽኑ ቅጣት የተላለፈባቸው አቶ ኤፍሬም አበራ እንደገለፁት የይግባኝ ሂደቱ ጉዳይ በቅርቡ እንደሚጀምሩና ቅጣቱ ከራሳቸው ይልቅ ክለቡ እንደሚለከተው ገልፀዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡