ከፍተኛ ሊግ| የየምድቦቹ አሸናፊዎች ዋንጫቸውን ሲረከቡ ውድድሩ ቅዳሜ ይጠናቀቃል

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የመጨረሻ (22ኛ ሳምንት) ሦስት ጨዋታዎች እሁድ ተካሂደው የየምድቡ አሸናፊዎች ዋንጫቸውን ሲረከቡ ቀሪዎቹ ጨዋታዎች ቅዳሜ ይደረጋሉ ተብሏል።

በምድብ ሀ ወልዲያን የገጠመው ሰበታ ከተማ 2-1 አሸንፏል። ለምድብ ሀ አሸናፊዎቹ ናትናኤል ጋንቹላ እና ብሩክ ሀዱሽ ጎሎቹን ሲያስቆጥሩ ተስፋዬ ነጋሽ የወልዲያ ብቸኛ ጎል ባለቤት ነው።

ሌሎች የምድብ ሀ ጨዋታዎች ቅዳሜ ሰኔ 29 ቀን 2011 በተመሳሳይ 4:00 ላይ ይደረጋሉ

አውስኮድ ከ ቡራዩ ከተማ
ፌዴራል ፖሊስ ከ አክሱም ከተማ
ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ወሎ ኮምቦልቻ
አቃቂ ቃሊቲ ከ ለገጣፎ ለገዳዲ
ገላን ከተማ ከ ደሴ ከተማ

በምድብ ለ ወልቂጤ ላይ ኢትዮጵያ መድን በአሰልጣኝ ያሬድ ቶሌራ እየተመራ የምድቡ አሸናፊ ወልቂጤ ከተማን 3-2 ማሸነፍ ችሏል። በ7ኛው ደቂቃ አቤል ማርቆስ መድንን ቀዳሚ ሲያደርግ ሐብታሙ ታደሰ በ20ኛው እና በ38ኛው ደቂቃ አከታትሎ ባስቆጠራቸው ጎሎች ወልቂጤን መሪ አድርጓል። ሆኖም ብዙም ሳይቆይ አብዱለጢፍ ሙራድ በ44ኛው እና 51ኛው ደቂቃዎች ሁለት ጎሎች አስቆጥሮ መድንን አሸናፊ አድርጓል።

የምድቡ ቀሪ ጨዋታዎች ቅዳሜ ሰኔ 29 ቀን 2011 (ከአንድ ጨዋታ በቀር) በተመሳሳይ 4:00 ላይ ይደረጋሉ።

ድሬዳዋ ፖሊስ ከ የካ ክ/ከተማ
ዲላ ከተማ ከ አዲስ አበባ ከተማ
ኢኮስኮ ከ ሀላባ ከተማ (9:00)
ናሽናል ሴሜንት ከ ሶዶ ከተማ
ሀምበሪቾ ዱራሜ ከ ነጌሌ አርሲ

የምድብ ሐ አሸናፊው ሀዲያ ሆሳዕና በሜዳው ጅማ አባ ቡናን 3-0 አሸንፏል። ጋናዊው መሐመድ ራዚቅ፣ እዩኤል ሳሙኤል እና ፍራኦል መንግስቱ የጎሎቹ ባለቤቶች ናቸው።

ሌሎች የምድቡ ጨዋታዎች ቅዳሜ ሰኔ 29 ቀን 2011 በተመሳሳይ 4:00 ላይ ይደረጋሉ።

ካፋ ቡና ከ ካምባታ ሺንሺቾ
ነጌሌ ቦረና ከ ቤንች ማጂ ቡና
ነቀምት ከተማ ከ ስልጤ ወራቤ
ሻሸመኔ ከተማ ከ ቡታጅራ ከተማ
ቢሾፍቱ አውቶ. ከ አርባምንጭ ከተማ


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡