የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የመጨረሻ (22ኛ ሳምንት) ቀሪዎቹ ጨዋታዎች እሁድ ተካሂደው የየምድቡ ወራጅ ቡድኖች ተለይተው ታውቀዋል።
በምድብ ሀ
ሰበታ ከተማ አሸናፊ በሆነበት ምድብ የአቃቂ እና የቡራዩ ላለመውረድ ሲያደርጉት የነበረው ትንቅንቅ ፍፃሜውን አግኝቷል። አቃቂ ቃሊቲ ለገጣፎ ለገዳዲን በዮናስ ባቢና ብቸኛ ግብ በማሸነፍ ሊጉ ላይ መቆየቱን አረጋግጧል። ወደ ባህር ዳር ያመራው ቡራዩ ከተማ አውስኮድን 2-1 ቢያሸነፍም ከመውረድ ግን አልተረፈም። በምድብ ሀ ቡራዩ በ25 ነጥብ እንዲሁም አውስኮድ በ 17 ነጥብ ወደ ይዘው ወደ አንደኛ ሊግ ወርደዋል።
አጠቃላይ የምድብ ሀ 22ኛ ሳምንት ጨዋታዎች
ሰበታ ከተማ 2-1 ወልዲያ
አቃቂ ቃሊቲ 1-0 ለገጣፎ ለገዳዲ
ገላን ከተማ 2-1 ደሴ ከተማ
ፌዴራል ፖሊስ 3-0 አክሱም ከተማ
አውስኮድ 1-2 ቡራዩ ከተማ
ኢትዮ ኤሌክትሪክ 3-2 ወሎ ኮምቦልቻ
ምድብ ለ
ወልቂጤ አንደኛ ሆኖ ባጠናቀቀበት ምድብ ለ ቀድሞ ድሬዳዋ ፖሊስ መውረዱን ያረጋገጠ ሲሆን ዛሬ ሌላኛው የድሬዳዋ ቡድን ናሽናል ሴሜንት ከወላይታ ሶዶ ጋር 2-2 መለያየቱን ተከትሎ ወደ አንደኛ ሊግ የወረደ ቡድን ሆኗል።
አጠቃላይ የምድብ ለ 22ኛ ሳምንት ጨዋታዎች
ወልቂጤ ከተማ 2-3 ኢትዮጵያ መድን
ድሬዳዋ ፖሊስ 3-5 የካ ክ/ከተማ
ሀምበሪቾ 3-0ገሌ አርሲ
ዲላ ከተማ 1-2 አዲስ አበባ ከተማ
ናሽናል ሴሜንት 2-2 ወላይታ ሶዶ ከተማ
ኢኮስኮ 5-1 ሀላባ ከተማ
ምድብ ሐ
ሀድያ ሆሳዕና አሸናፊ በሆነበት በዚህ ምድብ ቀድሞ መውረዱን ያረጋገጠው ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ሲሆን ከካፋ ቡና፣ ቡታጅራ እና ከነገሌ ቦረና አንደኛቸው የመውረድ እጣ ፈንታ ለነገሌ ቦረና ደርሶታል። ገሚሱ ጨዋታ በፎርፌ በተጠናቀቀው በዚህ ሳምንት ነገሌ ቦረና እና ካፋ ቡና ሶስት ነጥብ እና ሶስት ጎሎችን ያለ ልፋት ሲያገኙ ቡታጅራ ከሻሸመኔ አቻ ተለያይቷል። በዚህም መሰረት ቡታጅራ ከነገሌ ቦረና እኩል 24 ነጥብ በመያዝ በግብ ክፍያ በመብለጥ በሊጉ መቆየቱን አረጋግጧል።
አጠቃላይ የምድብ ለ 22ኛ ሳምንት ጨዋታዎች
ሀዲያ ሆሳአዕና 3-0 ጅማ አባ ቡና
ሻሸመኔ ከተማ 1-1 ቡታጅራ ከተማ
ነጌሌ ቦረና 3-0 ቤንችማጂ ቡና (ፎርፌ)
ቢሾፍቱ አውቶ. 0-2 አርባምንጭ ከተማ
ካፋ ቡና 3-0 ከምባታ ሺንሺቾ (ፎርፌ)
ነቀምት ከተማ 3-0 ስልጤ ወራቤ (ፎርፌ)
ስንታየሁ መንግስቱ የከፍተኛ ግብ አስቋጣሪነቱን በ15 ግቦች በማስቆጠር አጠናቋል።
© ሶከር ኢትዮጵያ
በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡