የኢትዮጵያ ዋንጫ ጨዋታዎች ሐሙስ ይደረጋሉ

በተዘበራረቀ መልኩ እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ዋንጫ (ጥሎ ማለፍ) ሦስት ጨዋታዎች ሐሙስ እንደሚደረጉ ታውቋል።

ከታኅሳስ ጀምሮ እየተካሄደ በሚገኘው የዘንድሮው ውድድር ከ16 የፕሪምየር ሊግ ክለቦች አራቱ ራሳቸውን ሲያገሉ ሦስት ጨዋታዎች ብቻ ተደርገዋል። በዚህም ኢትዮጵያ ቡና ሁለት ተከታታይ ፎርፌዎች አግኝቶ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ሲያልፍ ቀሪ አንድ የመጀመርያ ዙር እና ሦስት የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ተደርገው የመጨረሻ አራት ቡድኖች የሚለዩ ይሆናል።

አስቀድሞ በወጣው ድልድል መሠረት በአንደኛው ዙር ያልተደረገው ብቸኛው ጨዋታ በአዳማ ከተማ እና ባህር ዳር ከተማ መካከል ሐሙስ ሐምሌ አራት በአዳማ አበበ ቢቂላ 10;00 የሚደረግ ሲሆን ሁለት የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎችም በዚሁ ዕለት ይደረጋሉ። በፎርፌ ራሱን ከውድድሩ ያገለለው ደቡብ ፖሊስን አሸንፎ ወደ ሩብ ፍፃሜ ያለፈው የሊጉ ቻምፒዮን መቐለ 70 እንደርታ በሜዳው ከመከላከያ በ9:00 ሲጫወት ጅማ እና ድሬዳዋን በፎርፌ አሸንፈው የመጡት ወላይታ ድቻ እና ሀዋሳ ከተማ አዳማ ላይ በ8:00 የሚጫወቱ ይሆናል።

የውድድሩ አጠቃላይ ሒደት ይህንን ይመስላል

የ1ኛ ዙር ውጤቶች

ስሑል ሽረ
2-2 ሲዳማ ቡና (ሽረ በመለያ ምት አሸንፏል)

መከላከያ
1-0 ቅዱስ ጊዮርጊስ
ወልዋሎ ዓ.ዩ. 0-1 ፋሲል ከነማ

ኢትዮጵያ ቡና
3-0 ደደቢት (ፎርፌ)

ወላይታ ድቻ
3-0 ጅማ አባ ጅፋር (ፎርፌ)

መቐለ 70 እንደርታ
3-0 ደቡብ ፖሊስ (ፎርፌ)

ሀዋሳ ከተማ
3-0 ድሬዳዋ ከተማ (ፎርፌ)

ሀሙስ ሐምሌ 4 ቀን 2011
አዳማ ከተማ 10:00 ባህር ዳር ከተማ (አዳማ)

የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች

ኢትዮጵያ ቡና 3-0 ስሑል ሽረ (ፎርፌ)

ሐሙስ ሐምሌ 4 ቀን 2011

ሀዋሳ ከተማ 08:00 ወላይታ ድቻ (አዳማ)
መቐለ 70 እንደርታ 09:00 መከላከያ (መቐለ)

ቀኑ ወደ ፊት የሚገለፅ

አዳማ/ባህር ዳር ከ ፋሲል ከተማ

የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች
(ቀናት ወደፊት ይገለፃሉ)
ሀዋሳ/ድቻ ኢትዮጵያ ቡና
አዳማ/ባህርዳር/ፋሲል መቐለ/መከላከያ


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡