ቻን 2020| ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 25 ተጫዋቾች ተጠርተዋል

ኢትዮጵያ አስተናጋጅነቷን ያጣችበት የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) በ2020 መጀመርያ ካሜሩን ላይ ይስተናገዳል፡፡ ለዚሁ ውድድር የቅድመ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታ ከጅቡቲ የተደለደለችው ኢትዮጵያ ሀምሌ 19 ጅብቲ ላይ የመጀመሪያ ጨዋታዋን ታደርጋለች፡፡

አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ እና ረዳቶቹ በመሆን 25 ተጫዋቾች ያሳወቁ ሲሆን ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ አዳማ ላይ ዝግጅቱን ይጀምራል፡፡ ቡድኑ የመጀመሪያ ማጣሪያውን ከሜዳው ውጪ ካደረገ በኃላ የመልሱን መርሀ ግብር ኦገስት 4 ባህርዳር አልያም ድሬዳዋ ላይ ጨዋታውን ሊያደርግ እንደሚችል ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡

የተመረጡ 25 ተጫዋቾች ስም ዝርዝር

ግብ ጠባቂዎች፡ መሳይ አያኖ (ሲዳማ ቡና)፣ ተክለማርያም ሻንቆ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ምንተስኖት አሎ (ባህር ዳር ከተማ)

ተከላካዮች፡ አስቻለው ታመነ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ደስታ ደሙ (ወልዋሎ)፣ ያሬድ ባዬ (ፋሲል ከነማ)፣ ወንድሜነህ ደረጀ (ባህር ዳር ከተማ)፣ አህመድ ረሺድ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ጌቱ ኃይለማርያም (ሰበታ ከተማ)፣ አምሳሉ ጥላሁን (ፋሲል ከነማ)፣ ረመዳን የሱፍ (ስሑል ሽረ)

አማካዮች፡ አማኑኤል ዮሐንስ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ሙሉዓለም መስፍን (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ሀይደር ሸረፋ (መቐለ)፣ አፈወርቅ ኃይሉ (ወልዋሎ)፣ ሱራፌል ዳኛቸው (ፋሲል ከነማ)፣ ታፈሰ ሰለሞን (ሀዋሳ ከተማ)፣ ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን (ሀዋሳ ከተማ)

አጥቂዎች፡ አቤል ያለው (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ሀብታሙ ገዛኸኝ (ሲዳማ ቡና)፣ አማኑኤል ገብረሚካኤል (መቐለ)፣ አቡበከር ነስሩ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ሙጂብ ቃሲም (ፋሲል ከነማ)፣ ፍቃዱ ዓለሙ (መከላከያ)፣ አዲስ ግደይ (ሲዳማ ቡና)


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡