የአንደኛ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር ዕሁድ ይጀምራል

በስድስት ምድቦች ተከፍሎ በኅዳር ወር መጀመሪያ በ58 ክለቦች መካከል ሲደረግ የቆየው የአንደኛ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር ከፊታችን ዕሁድ ጀምሮ በባቱ (ዝዋይ) ከተማ ይጀመራል፡፡

ሁሉም የምድብ ጨዋታዎች ባሳለፍነው ሳምንት የተጠናቀቁ ሲሆን ወደ ከፍተኛ ሊግ የሚገቡ ስድስት ክለቦችን የሚለየው የማጠቃለያ ጨዋታ ደግሞ ቅዳሜ የዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት ከተካሄደ በኋላ ዕሁድ ውድድሩ በይፋ የሚጀመር መሆኑን ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡

ከየምድባቸው ያለፉ ተሳታፊ 18 ክለቦች

ከምድብ ሀ፡ ሱሉልታ ከተማ፣ መቱ ከተማ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ

ከምድብ ለ፡ ባቱ ከተማ፣ ቢሾፍቱ ከተማ፣ መተሀራ ስኳር

ከምድብ ሐ፡ ዳሞት ከተማ፣ የጁ ፍሬ ወልዲያ፣ ላስታ ላሊበላ

ምድብ መ፡ ሶሎዳ ዓድዋ፣ ናኖ ሁርቡ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ

ምድብ ሠ፡ ራያ አዘቦ፣ ሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን፣ አዲስ አበባ ፖሊስ

ምድብ ረ፡ ጋሞ ጨንቻ፣ ቡሌ ሆራ፣ ጎፋ ባራንቼ


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡