አዳማ ከተማ የቀድሞ አሰልጣኙን መልሷል


አዳማ ከተማዎች የቀድሞ አሰልጣኛቸው አሸናፊ በቀለን በድጋሚ ለመቅጠር መወሰናቸውን ተከትሎ አሰልጣኙም ሥራቸውን ከወዲሁ መጀመራቸው እየተነገረ ይገኛል።

ለቀጣይ ውድድር ዓመት አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር የአዳማ ከተማ የሥራ አስፈፃሚ አባላት ሦስት አሰልጣኞችን ማለትም አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ፣ ግርማ ሐብተዮሐንስ እና አሸናፊ በቀለን ለመጨረሻ አሰልጣኝነት እጩነት ካቀረቡ በኋላ አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለን አሰልጣኝ አድርጎ ለመሾም መወሰናቸው ታውቋል። (አሰልጣኞቹ ለእጩነት የቀረቡት የስራ ማመልከቻ አስገብተው ሳይሆን ክለቡ ለስራው ይሆኑኛል ብሎ በእጩነት በመያዙ እንደሆነ ልብ ይሏል)

አሁን እየወጡ እንዳሉት መረጃዎች ከሆነም አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ከቡድኑ ጋር ሥራቸውን የጀመሩ ሲሆን ለቀጣይ ዓመት ቡድኑን ለማጠናከር በማሰብ ተጫዋቾችን ለማስፈረም እየተነጋገሩ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል።

ከዚ በፊት ከ2006 እስከ 2009 የአዳማ ከተማ አሰልጣኝ ሆነው የሰሩት አሸናፊ በቀለ ላለፉት ስድስት ወራት በወላይታ ድቻ ጥሩ የሚባል ቆይታ ማድረጋቸው ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡