ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ተጋጣሚዎቿን አውቃለች

በ2021 በካሜሩን አስተናጋጅነት ለሚከናወነው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የምድብ ድልድል ይፋ ሆኗል።

የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫን እያስተናገደች በምትገኘው የግብፅ መዲና ካይሮ በተካሄደው የዕጣ ማውጣት ሥነ-ሥርዓት ኢትዮጵያ በምድብ 11 ከጠንካራዋ አይቮሪኮስት፣ ከዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ክስተት ማዳጋስካር እና ኒጀር ጋር ተደልድላለች።

የአፍሪካ ዋንጫው 12 ምድቦች የሚኖሩት ሲሆን አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ይዘው ከሚጨርሱ ብሔራዊ ቡድኖች ከሁለት ዓመት በኋላ ለሚደረገው የአፍሪካ ዋንጫ የሚያልፉ ይሆናል።

ምድብ 1 – ማሊ፣ ጊኒ፣ ናሚቢያ፣ ላይቤሪያ

ምድብ 2 – ቡርኪና ፋሶ፣ ዩጋንዳ፣ ማላዊ፣ ደቡብ ሱዳን/ሲሸልስ

ምድብ 3 – ጋና፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሱዳን፣ ሞሪሸስ/ሳኦቶሜ

ምድብ 4 – ኮንጎ ዲሪ.፣ ጋቦን፣ አንጎላ፣ ጅቡቲ/ጋምቢያ

ምድብ 5 – ሞሮኮ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ፣ ቡሩንዲ፣ ሞሪታንያ

ምድብ 6 – ካሜሩን፣ ሞዛምቢክ፣ ሩዋንዳ፣ ኬፕ ቨርድ

ምድብ 7 – ግብፅ፣ ኬንያ፣ ቶጎ፣ ኮሞሮስ

ምድብ 8 – አልጄርያ፣ ዚምባብዌ፣ ቦትስዋና፣ ዛምቢያ

ምድብ 9 – ሴኔጋል፣ ኮንጎ፣ ጊኒ ቢሳዋ፣ ኢስዋቲኒ

ምድብ 10 – ቱኒዚያ፣ ሊቢያ፣ ታንዛኒያ፣ ኢኳ. ጊኒ

ምድብ 11 – አይቮሪኮስት፣ ኢትዮጵያ፣ ኒጀር፣ ማዳጋስካር

ምድብ 12 – ናይጄርያ፣ ሴራ ሊዮን፣  ቤኒን፣ ሌሶቶ


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡