ወደ ከፍተኛ ሊግ ያደጉ ቡድኖች በሙሉ ሲታወቁ ኮልፌ ቀራኒዮ እና ባቱ ከተማ ለፍፃሜ ደርሰዋል

የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር የግማሽ ፍፃሜ እና ወደ ከፍተኛ ሊግ ለመግባት የመለያ ጨዋታዎች ዛሬ ተከናውነው ወደ ከፍተኛ ሊግ ያደጉ ቡድኖች በሙሉ ተለይተዋል። ኮልፌ ቀራኒዮ እና ባቱ ከተማም የዋንጫ ተፋላሚዎች ሆነዋል።

03:00 ላይ አዲስ አበባ ፖሊስን ከ ሰሜን ሸዋ ደብረብርሀን ያገናኘው የመለያ ጨዋታ በደ/ብርሀን 2-0 አሸናፊነት ተጠናቋል። በዚህም በ2009 ወደ አንደኛ ሊጉ ወርዶ የነበረው ደ/ብርሀን ወደ ከፍተኛ ሊግ መመለሱን አረጋግጧል።

05:00 ላይ በቀጠለው የመለያ ጨዋታ ቂርቆስ ክ/ከተማ ሱሉልታ ከተማን 2-1 በማሸነፍ ወደ ከፍተኛ ሊግ ማደጉን አረጋግጧል። ቂርቆስ ወደ ከፍተኛ ሊግ ሲያድግ ይህ ለመጀመርያ ጊዜ ነው።

ዛሬ በተካሄዱት የመለያ ጨዋታዎች የተመዘገቡትን ውጤቶች ጨምሮ የሚከተሉት ስድስት ቡድኖች ወደ ከፍተኛ ሊግ አድገዋል።

– ሶሎዳ ዓድዋ
– ኮልፌ ቀራኒዮ
– ጋሞ ጨንቻ
– ባቱ ከተማ
– ሰ/ሸ/ደ/ብርሃን
– ቂርቆስ ክ/ከተማ

07:00 ላይ በግማሽ ፍፃሜው ሶሎዳ ዓድዋ እና ኮልፌ ቀራኒዮ ያደረጉት ጨዋታ በመደበኛው ክፍለ ጊዜ 1-1 ተጠናቆ በመለያ ምቶች ኮልፌ 4-3 አሸንፎ ለፍፃሜ ደርሷል።

9:00 ላይ በሌላኛው የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ባቱ ከተማ እና ጋሞ ጨንቻ ያደረጉት ጨዋታ በተመሳሳይ በመደበኛው ክፍለ ጊዜ ያለ ጎል ተጠናቆ በተሰጡ የመለያ ምቶች ባቱ ከተማ 6-5 አሸንፎ ለፍፃሜ አልፏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡