ኢትዮጵያ የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ ተጋጣሚዋን አውቃለች

የ2022 የዓለም ዋንጫ የአፍሪካ ዞን የማጣርያ ድልድል ዛሬ ሲወጣ ኢትዮጵያ በቅድመ ማጣርያው ከሌሶቶ ጋር ተደልድላለች።

28 ሀገራት እርስ በእርስ በሚፋለሙበት በዚህ ቅድመ ማጣርያ ውድድር 14 አሸናፊ ሀገራት ወደ ምድብ ማጣርያው የሚገቡ ሲሆን ኢትዮጵያም ደቡባዊ አፍሪካዊቷ ሀገር ሌሶቶን የምትገጥም ይሆናል። የመጀመርያ ጨዋታው ነሐሴ 26 በኢትዮጵያ ሜዳ ሲከናወን የመልሱ ጨዋታ ደግሞ በሳምንቱ ሌሶቶ ላይ የሚከናወን ይሆናል።

ሁለቱ ሀገራት ለ2017 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ በአንድ ምድብ እንደነበሩ የሚታወስ ሲሆን ባህር ዳር ላይ በተደረገው ጨዋታ ኢትዮጵያ በጋቶች ፓኖም እና ሳላዲን ሰዒድ ጎሎች 2-1 ስታሸንፍ በተመሳሳይ ሌሶቶ ላይም በጌታነህ ከበደ ሁለት ጎሎች ኢትዮጵያ 2-1 ማሸነፏ የሚታወስ ነው።

የቅድመ ማጣርያው ሙሉ ድልድል ይህንን ይመስላል

ኢትዮጵያ ከ ሌሶቶ
ሶማሊያ ከ ዚምባብዌ
ኤርትራ ከ ናሚቢያ
ቡሩንዲ ከ ታንዛኒያ
ጅቡቲ ከ ኢስዋቲኒ
ቦትስዋና ከ ማላዊ
ጋምቢያ ከ አንጎላ
ላይቤርያ ከ ሴራሊዮን
ሞሪሸስ ከ ሞዛምቢክ
ሳኦቶሜ ከ ጊኒ ቢሳው
ደቡብ ሱዳን ከ ኢኳቶርያል ጊኒ
ኮሞሮስ ከ ቶጎ
ቻድ ከ ሱዳን
ሲሸልስ ከ ሩዋንዳ


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡