አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ከቢጫ ለባሾቹ ጋር ለመቆየት ከጫፍ መድረሳቸው ታውቋል።
ባለፈው ዓመት ከድሬዳዋ ከተማ ከተለያዩ በኋላ ከወልዋሎ ጋር ቆይታ ያደረጉት አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ከወልዋሎ ጋር የነበራቸው ውል መጠናቀቁን ተከትሎ የአሰልጣኙ መዳረሻ የት ይሆናል የሚለው መነጋገርያ ነበር። ከአዳማ ከተማ እና ከባህር ዳር ከተማ ጋር በስፋት ስማቸው ሲያያዝ የቆየው አሰልጣኙ በቀጣይ ቀናት ባለፉት ስድስት ወራት ቆይታ ባደረጉበት ወልዋሎ ጋር ውላቸውን የሚያድሱበት ዕድል የሰፋ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
አሰልጣኙ ባለፈው ጥር ወር ወልዋሎ ከተቀላቀሉ በኋላ ቡድኑ ከበርካታ ዓመታት በኋላ ወደሚታወቅበት ታዳጊዎች የማሳደግ ባህሉ እንዲመለስ እና ወጪ እንዲቆጥብ ጥረቶች በማድረጋቸው በክለቡ አመራሮች ተቀባይነት አግኝተዋል።
© ሶከር ኢትዮጵያ
በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡