ስሑል ሽረ ቅጣት ተላለፈበት

ስሑል ሽረ ከወልዋሎ ጋር በነበረው ጨዋታ የሽረ ደጋፊዎች ያልተገባ ድርጊት ፈፅመዋል ያለው የፌዴሬሽኑ ዲሲፕሊን ኮሚቴ በክለቡ ላይ ቅጣት ጥሏል፡፡

በ2011 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 29ኛው ሳምንት ትግራይ ስታዲየም ላይ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከስሑል ሽረ ባደረጉት ጨዋታ ስሑል ሽረ 2-1 ማሸነፉ ይታወሳል፡፡ የፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን ኮሚቴም በጨዋታው ላይ የስሑል ሽረ ደጋፊዎች በተፈጠረው ረብሻ ከፍተኛ ላይ አስተዋጽኦ ነበራቸው በማለት ቅጣት አስተላልፏል፡፡ በዚህም መሠረት በ2012 የውድድር ዘመን 3 የሜዳው ጨዋታዎችን ከከተማው 300 ኪ/ሜ ርቆ እንዲጫወት እና 120 ሺህ ብር እንዲከፍል ተወስኖበታል።

የቅጣት ደብዳቤ👇


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡