የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ያዘጋጀው በኢትዮጵያ እግርኳስ የሚታየውን የሊግ ውድድር የአደረጃጀት ችግሮች በመለየትና የመፍትሔ ሀሳቦች በማስቀመጥ ላይ ያተኮረ ጥናት ዛሬ በሸራተን አዲስ ሆቴል የአአ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተወካይ፣ አአ የስፖርት ኮሚሽን ኃላፊዎች፣ የአአ የስራ አስፈፃሚ አባላት እንዲሁም የ22 ክለቦች ፕሬዝዳንቶች በተገኙበት ለውይይት ቀርቧል።
በቀረበው ጥናት ዙርያ ተጨማሪ ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኃላ በመጨረሻም በዕለቱ የተገኙ ክለቦች ለእግርኳሱ ዕድገትም ሆነ አላግባብ የሚወጡ የመንግስት የገንዘብ ወጪ ላማስቀረት በማሰብ ከዚህ በኋላ (ከ2012 ጀምሮ) በአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ስር በመሆን ለመወዳደር በጋራ ተስማምተው ተፈራርመዋል።
ስምምነታቸውንም የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለሚመለከተው አካላት በሙሉ እንዲያደርስ ወስነው ጉባዔው ተጠናቋል።
የጉባዔውን ዝርዝር እንደደረሰን እናቀርባለን
© ሶከር ኢትዮጵያ
በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡