የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር በጋራ በመሆን በተጫዋቾች ዝውውር እና የክፍያ መጠን ያተኮረ ስብሰባ ዓርብ ነሐሴ 3ቀን ከ03:00 ጀምሮ ቢሾፍቱ ከተማ ላይ ሊካሄድ ነው።
በስብሰባው ላይ የክልል ከ/አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽኖች እና እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንቶች ፣ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ አባላት፣ 16ቱ የፕሪምየር ሊግ ክለቦች እና አዲስ አዳጊ ሦስት ቡድኖች ፕሬዝደንቶች እንዲሁም ስራ አስኪያጅ፣ የዳኞችና ኮሚሽነሮች ማኅበር እና የአሰልጣኞች ማኅበር ተወካዮች እንዲገኙ ጥሪ ተላልፏል።
የአሰልጣኝ እና የተጫዋች ዝውውር በከፍተኛ ሁኔታ እየተካሄደ በሚገኝበት በአሁኑ ሰዓት ስብሰባው ዘግይቶ መጠራቱ በቀጣይ ምን ዓይነት ለውጥ ይፈጥራል የሚለው ተጠባቂ መሆኑ እንዳለ ሆነ የጉዳዩ ባለቤት የሆኑት ተጫዋቾች ተወካዮች አለመካተታቸው ጥያቄ አስነስቷል።
© ሶከር ኢትዮጵያ
በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡