የ2011 የተጫዋቾች ከፍተኛ እና ዝቅተኛ ደሞዝ መጠን…

የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ደሞዝ ጣርያን በመገደብ ዙርያ ዛሬ በቢሾፍቱ ከተማ በተካሄደው ስብሰባ ላይ በቀረበ ጥናታዊ ፅሁፍ የፕሪምየር ሊግ ክለቦች በ2011 የከፈሉት ከፍተኛ እና ዝቅተኛ ደሞዝ ይፋ ሆኗል።

በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን የክለብ ላይሰንሲንግ ማናጀር የሆኑት ተድላ ዳኛቸው ዛሬ ለቀረበው የውይይት አጀንዳ መነሻ የሆነ ጥናታዊ ፅሁፍ ባቀረቡበት ወቅት የተጫዋቾች ወቅታዊ ከፍተኛ እና ዝቅተኛ ደሞዝን ጠቅሰዋል። በጥናቱ መሰረት በ2011 የውድድር ዓመት በኢትዮጵያ ሦስቱ ከፍተኛ የሊግ እርከኖች የሚከፈለው አማካይ ወርሃዊ የደሞዝ ክፍያ ይንን ይመስላል።

*ፕሪምየር ሊግ
-ዝቅተኛ – 43,000ብር
-ከፍተኛ – 304, 000ብር

*ከፍተኛ ሊግ
-ዝቅተኛ – 5,000ብር
-ከፍተኛ – 20,000ብር
*በአንደኛ ሊግ
-ዝቅተኛ – 2,500ብር
-ከፍተኛ – 3,500ብር

በ2011 የውድድር ዓመት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች ለአንድ ተጫዋች የከፈሉት ከፍተኛና ዝቅተኛ ደሞዝ ደግሞ ይህንን ይመስላል።

(ዝ-ዝቅተኛ / ከ-ከፍተኛ)

ጅማ አባ ጅፋር፡ ዝ-15,000 ከ-304,000

ፋሲል ከነማ፡ ዝ-5000 ከ-189,000

ሲዳማ ቡና፡ ዝ-74,000 ከ-213,000

ሀዋሳ ከተማ: ዝ-150,000 ከ-166,000

ቅዱስ ጊዮርጊስ፡ ዝ-3,000 ከ-100,000

አዳማ ከተማ፡ ዝ-3000 ከ-228,000

መከላከያ፡ ዝ-3,100 ከ-182,000

ደደቢት፡ ዝ-10,000 ከ-25,000

ወላይታ ድቻ፡ ዝ-5,000 ከ-155,000

ድሬዳዋ ከተማ፡ ዝ-5000 ከ-175,000

ወልዋሎ፡ ዝ-15,000 ከ-166,000

መቐለ 70 እንደርታ፡ ዝ-73,000 ከ-190,000

ደቡብ ፖሊስ፡ ዝ-6,000 ከ-27,000

ስሁል ሽረ፡ ዝ-10,000 ከ-105,000

ባህር ዳር ከተማ፡ ዝ-45,000 ከ-151,000

*ኢትዮጵያ ቡና፡ በጥናቱ ማብራሪያ ወቅት አልተጠቀሰም።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡