የደሞዝ ጣርያን ለመወሰን የተጠራው ስብሰባ ወደ ሌላ ቀን ተሸጋገረ

ባሳለፍነው ሳምንት የፕሪምየር ሊጉ ተጫዋቾች የደሞዝ ጣርያን ለመገደብ ከውሳኔ የደረሰው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በተመሳሳይ በከፍተኛ ሊግ እና አንደኛ ሊግ ላይም ውሳኔ ለማሳለፍ የጠራው ስብሰባ ዛሬ ሳይካሄድ ቀርቷል።
ዓለምገና በሚገኘው አንኳር ሆቴል በተጠራው ስብሰባ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ጂራ እና ፀኃፊው ኢያሱ መርሐፅድቅ (ዶ/ር) የተገኙ ሲሆን የክለብ ተወካዮች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በበቂ ሁኔታ ባለመገኘታቸው ምክንያት ወደ ነሐሴ 25 እንዲሸጋገር ከስምምነት ተደርሷል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡