የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የማጠቃለያ ውድድር በስድስት ቡድኖች መካከል ከነሐሴ 5-15 ድረስ በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የመክፈቻ ጨዋታዎችም ነገ ይደረጋሉ።
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች እና የተሳታፊ ክለቦች ተወካዮች በተገኙበት 09:00 ላይ በአዳማ የስብሰባ አዳራሽ ውድድሩን አስመልክቶ ውይይት ተደርጓል። ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ መድን ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና አዲስ አበባ ከተማ የማይሳተፉ ቡድኖች መሆናቸውም ታውቋል። በዚህም መሠረት ውድድሩ በምን መልኩ ይካሄድ (በሁለት ምድብ ሦስት ሦስት ቡድን ይድረግ ወይስ በአንድ ዙር በሚደረግ ጨዋታ አሸናፊው ይለይ) የሚለው ብዙ ክርክርና ውይይት ተደርጎበታል። በመጨረሻም ቢያንስ አንድ ቡድን ሁለት ጨዋታ አድርጎ ከሚመለስ አምስት ጨዋታ ማድረጉ የተሻለ ነው በሚል ተስማምተው በአንድ ዙር በሚደረግ ጨዋታ በነጥብ የተሻለ የሆነው ቡድን የውድድሩ አሸናፊ እንዲሆን በመስማማት የተጋጣሚ ቡድኖች መርሐግብር ወቷል።
ተሳታፊ ቡድኖች
አዳማ ከተማ ፣ አፍሮ ፅዮን ፣ ፋሲል ከነማ ፣ መከላከያ ፣ ወላይታ ድቻ እና ሀዋሳ ከተማ
የመክፈቻ ጨዋታዎች
እሁድ ነሐሴ 5 ቀን 2011
06:00 | አዳማ ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ
08:00 | አፍሮ ፅዮን ከ ወላይታ ድቻ
10:00 | ፋሲል ከነማ ከ መከላከያ
© ሶከር ኢትዮጵያ
በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡