ከፍተኛ ሊግ : ወልድያ ፣ አአ ከተማ እና አአ ፖሊስ 100% የማሸነፍ ሪኮርዳቸውን ይዘው ቀጥለዋል

በ32 ክለቦች መካከል በሁለት ምድብ ተከፍሎ እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 3ኛ ሳምንት ላይ ደርሷል፡፡ ትላንት እና ዛሬ በተደረጉ ጨዋታዎችም አአ ፖሊስ ፣ አአ ከተማ እና ወልድያ 100% የማሸነፍ ሪኮርዳቸውን ይዘው ሲቀጥሉ የጅማ ደርቢ በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡

ትላንት በተደረጉት የምድብ ለ ሁለት ጨዋታዎች ፌዴራል ፖሊስ ከ ደቡብ ፖሊስ 2-2 አቻ ውጤት ሲለያዩ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከርሲ ነገሌ 1-1 አቻ ተለያይተዋል፡፡

ቀሪዎቹ የሊጉ 14 ጨዋታዎች ዛሬ በተለያዩ ከተሞች ሲካሄድ ከፍተና ግምት ተሰጥቶት የነበረው በጅማ ከነማ እና ጅማ አባቡና መካከል የተደረገው የጅማ ደርቢ ካለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡ በተመሳሳይ በምድብ ሀ ጠንካራ ፍልሚያ ይደረግበታል ተብሎ የተጠበቀው የፋሲል ከተማ እና ወሎ ኮምቦልቻ የፋሲለደስ ስታድየም ፍልሚያ 0-0 ተጠናቋል፡፡ መድን ሜዳ ላይ ወልድያን ያስተናገደው መድን 2-0 ተሸንፏል፡፡ ባለፈው ሳምንት ባስቆጠረው ብቸኛ ግብ ወልድያን ለድል የመራው እዮብ ወ/ማርያም ዛሬም ባስቆጠራቸው ሁለት ግቦች ወልድያ ከ3 ጨዋታ ሙሉ 9 ነጥብ እንዲሰበስብ አድርጓል፡፡

ወደ ድሬዳዋ ያቀናው አዲስ አበባ ከተማ በድል የውድድር ዘመን ጅማሮውን አሳምሯል፡፡ የአሰልጣኝ ስዩም ከበደ ቡድን በአቤል ዘውዱ እና ዳዊት ማሞ ግቦች ናሽናል ሴሜንትን 2-0 በማሸነፍ የምድብ ለን የደረጃ ሰንጠረዥ ለብቻው ተቆናጧል፡፡

ባህርዳር ከተማ ወደ ሰበታ ተጉዞ በዳንኤል ደምሴ ብቸኛ ግብ ሰበታ ከተማ ላይ ያልተጠበቀ ድል አስመዝግቦ ሲመለስ መቐለ ከተማ ወደ አሰላ ተጉዞ ሙገርን በክብሮም አስመላሽ እና ኃይሉ ገ/የሱስ ቦች 2-1 አሸንፎ ተመልሷል፡፡

አዲግራት ላይ አውስኮድን የገጠመው ወልዋሎ በመጨረሻ ደቂቃ በተቆጠረች ግብ ታግዞ 3-2 ሲያሸንፍ አዲስ አበባ ፖሊስ አበበ ቢቂላ ላይ ሰሜንሸዋ ደብረብርሃንን አስተናግዶ በአባይነህ ፌኖ ግቦች 2-0 በማሸነፍ የምድብ ሀ ሰንጠረዥን ከወልድያ ጋር እኩል ነጥብ መምራት ቀጥሏል፡፡  ተሸናፊው ደብረብርሃን ደግሞ የሰንጠረዡ ግርጌን ካለምንም ነጥብ ለመያዝ ተገዷል፡፡

በአጠቃላይ የ3ኛ ሳምንት ውጤቶች እና የደረጃ ሰንጠረዥ ይህንን ይመስላል፡-

ምድብ ሀ

ሱሉልታ ከተማ 2-3 ኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት

-ኤርሚያስ ታሪኩ         – ኄኖክ ታደሰ

-አቤል ታሪኩ             – ደጀኔ አድመ

– እዮብ ታደሰ

 

ሰበታ ከተማ 0-1 ባህርዳር ከተማ

-ዳንኤል ደምሴ

 

ኢትዮጵያ መድን 0-2 ወልድያ

-እዮብ /ማርያም (2)

 

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ 3-2 አማራ ውሃ ስራ

-አስተማርያም መሪ             – መለሰ ትዛዙ

-መኩርያ ደሱ                  –  ሐብታሙ ሸዋለም

-በርገና ባጫ

 

ሙገር ሲሚንቶ 1-2 መቐለ ከተማ

-ደስታ ደሙ             -ክብሮም አስመላሽ

-ኃይሉ ገ/እየሱስ

 

አአ ፖሊስ 2-0 ሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን

-አባይነህ ፌኖ

 

ፋሲል ከተማ 0-0 ወሎ ኮምቦልቻ

 

ቡራዩ ከተማ 0-0 አክሱም ከተማ

A standing

ምድብ ለ

ፌዴራል ፖሊስ 2-2 ደቡብ ፖሊስ

-ሃለፎም ኮሃስ       – ወንድሜነህ አይናለም (2)

-ቻላቸው ቤዛ

 

አአ ዩኒቨርሲቲ 1-1 አርሲ ነገሌ

-ኢዩኤል ንጉሴ      -አገኘሁ ልኬሳ

 

ጅንካ ከተማ 1-0 ሻሸመኔ ከተማ

-ሚሊዮን መንገሻ

 

ባቱ ከተማ 1-0 ነቀምት ከተማ

-ጀማል ራህመቶ

 

ናሽናል ሴሜንት 0-2 አዲስ አበባ ከተማ

-አቤል ዘውዱ

-ዳዊት ማሞ

ሀላባ ከተማ 0-0 ድሬዳዋ ፖሊስ

ነገሌ ቦረና 1-0 ወራቤ ከተማ

-አንተነህ አካለወልድ

B Standing

ያጋሩ