ጳውሎስ ጌታቸው አዲሱ የጅማ አባ ጅፋር አሰልጣኝ ሆነው ተሹመዋል።
ጅማ አባጅፋሮች ከዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ጋር ከተለያዩ በኋላ ለረጅም ጊዜያት በረዳቱ ዩሱፍ ዓሊ እየተመሩ ዓመቱን ያጠናቀቁ ሲሆን አሁን ደግሞ ከባህርዳር ከተማ ጋር ቆይታ ያደረጉት ጳውሎስ ጌታቸውን አሰልጣኝ አድርገው ቀጥረዋል።
ባለፈው ዓመት የመጀመርያ ዙር በባህር ዳር ከተማ ጠንካራ የተከላካይ ክፍል ያለው ቡድን የሰሩት አሰልጣኙ ቡድኑን በአንድ ዓመት ውል የተቀላቀሉ ሲሆን ጅማ አባጅፋሮች በድጋሚ የዋንጫ ተፎካካሪ ቡድን የማድረግ ኃላፊነት ይጠብቃቸዋል።
ከዚህ ቀደም ሀዲያ ሆሳዕና፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ ሱሉልታ ከተማ እና ባህር ዳር ከተማ የሰሩት አሰልጣኙ ቡድናቸው ለቀጣይ የውድድር ዓመት የማዘጋጀቱ ስራ ቀድመው ይጀምራሉ ተብሎ ሲጠበቅ እንደ ከዚ ቀደም ቡድኖቻቸው በአዲሱ ቡድናቸውም ለአጨዋወታቸው የሚመች ቡድን ይሰራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
© ሶከር ኢትዮጵያ
በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡