በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ በኤርትራ አዘጋጅነት የሚካሄደው የሴካፋ ዋንጫ ነገ በቺቾሮ ስታዲየም ሲጀመር በጅቡቲ መቅረት ምክንያት አዲስ ምድብ ወጥቷል።
ይህ ውድድር ነገ 8:00 ኬኒያ ከ ሶማሊያ በሚያደርጉት ጨዋታ ሲጀመር ከመክፈቻው ጨዋታ ቀጥሎም አዘጋጅዋ ኤርትራ ከብሩንዲ ጋር በምታደርገው ጨዋታ ይቀጥላል።
እስከ መጨረሻው ሰዓት ድረስ በውድድሩ ትሳተፋለች ተብላ ስትጠበቅ የነበረችው ጅቡቲ ከውድድሩ ራሷን ማግለሏን ተከትሎ ዛሬ ስድስት ሰዓት በሴካፋ ዋና ፀሃፊ ኒኮላስ ሚዜፔ አማካኝነት በምድብ ድልድሉ ላይ መጠነኛ ለውጥ ተደርጓል። በዚህም በሦስት ተከፍሎ የነበረው ምድብ ወደ ሁለት ዝቅ ብሎ በሦስተኛው ምድብ የነበሩ ሀገራት ወደ ሁለቱ ምድብ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል።
በውድድሩ ላይ የምትሳተፈው ኢትዮጵያ ነገ ወደ ስፍራው አቅንታ ከነገ በስቲያ የመጀመርያ ጨዋታዋን ከ ዩጋንዳ ጋር የምታከናውን ሲሆን ጉዞውን እና የቡድኑን ዝግጅት አስመልክቶ በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ እየተሰጠ ይገኛል።
የተሻሻለው የምድብ ድልድል ይህንን ይመስላል፡-
ምድብ አንድ
ኤርትራ
ብሩንዲ
ኬንያ
ሱዳን
ሶማሊያ
ምድብ ሁለት
ዩጋንዳ
ኢትዮጵያ
ታንዛንያ
ደቡብ ሱዳን
ሩዋንዳ
© ሶከር ኢትዮጵያ
በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡