አፍሪካ | ሚቾ እና ኦርላንዶ ፓይሬትስ ተለያዩ

ስማቸው ከፈረሰኞቹ ጋር ሲያያዙ የቆዩት ሰርቢያዊው የኦርላንዶ ፓይሬትስ አሰልጣኝ ሰርዮቪች ሚሉቲን “ሚቾ” ከደቡብ አፍሪካው ክለብ ጋር ተለያይተዋል።

ከዩጋንዳ ጋር ጥሩ ጊዜያትን ካሳለፉ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ የደቡብ አፍሪካው ክለብ ኦርላንዶ ፓይሬትስን ላለፉት ሁለት ዓመታት ያሰለጠኑት እኚህ አሰልጣኝ ዓርብ አመሻሽ ነው ራሳቸው ከክለቡ አሰልጣኝነት ያነሱት። ከሳምንታት በፊት በአሰልጣኙ ላይ ፍላጎት ያሳዩት እና እስካሁን ድረስ ዋና አሰልጣኝ ያልቀጠሩት ፈረሰኞቹም ሰርቢያዊው ወጣት አሰልጣኝ በድጋሚ የሚመልሱበት ዕድል እንዳለም ይገመታል።

ከዚ ቀደም በቅዱስ ጊዮርጊስ በሁለት ጊዜያት በነበረው ቆይታቸው ለአምስት ዓመታት የሊጉን ዋንጫ እንዲያነሳ ያስቻሉት አሰልጣኙ በሱዳኑ አል ሂላል ኦምዱርማን፣ በዩጋንዳው ቪላ እንዲሁም በዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን ጥሩ ጊዜያት አሳልፈዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡