የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን እና ስፓይን ስፓርት አማካሪ በጋራ ያዘጋጁት በመጀመርያ የህክምና እርዳታ ላይ ያተኮረ ስልጠና ትናንት ተጠናቀቀ።
በሁለቱም አካላት በጋራ የተዘጋጀው የመጀመርያ የህክምና ዕርዳታ አሰጣጥ የተመለከተ ስልጠና ላለፉት አራት ቀናት የተካሄደ ሲሆን በስልጠናውም ወጌሻዎች ፣ የክለብ አመራሮች እና በእግር ኳስ ዙርያ ያሉ ግለሰቦች ተሳትፈዋል። ለአራተኛ ግዜ የተሰጠው ይህ ስልጠና ዓላማው በእግር ኳስ ሜዳዎች የሚያጋጥሙ ጉዳቶት በቂ ህክምና ከማግኘታቸው በፊት የመጀመርያ ዕርዳታ ለማድረግ እና የሜዳ ላይ ጉዳቶት ለመቀነስ ነው ተብሏል።
ስልጠናው በብዛት የከፍተኛ ሊግ ባለሞያዎች ያሳተፈ ሲሆን በመጠናቀቅያው ቀንም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ እና ሌሎች በክብር እንግድነት የተገኙበት ነበር።
© ሶከር ኢትዮጵያ
በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡