ቻን 2016 : ወደሩብ ፍፃሜ የሚያልፉ ሃገራት እየተለዩ ነው

-ሩዋንዳ እና ኮትዲቯር ከምድብ 1 ወደ ሩብ ፍፃሜ አልፈዋል

በአፍሪካ ሃገራት ዋንጫ (ቻን) ኮትዲቯር ጋቦንን 4-1 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ ከምድብ አንድ ሩዋንዳን ተከትላ ያለፈች ቡድን ሆናለች፡፡ ለዝሆኖቹ የማሸናፊያውን ግቦቹን አካ ኢስስ፣ ጄጄ ጉይዛ፣ ኮፊ ቦአ እና ኒልማር ብሊ አስቆጥረዋል፡፡ ጋቦንን ከባዶ መሸነፍ የታደገች ግብ ፍራንክ ኦባምቦ በስሙ አስመዝግቧል፡፡

ሞሮኮ አስቀድማ ማለፏን ያረጋገጠችው ሩዋንዳን በተመሳሳይ 4-1 ብታሸንፍም ከምድብ ወድቃለች፡፡  አስተናጋጅዋ ሩዋንዳ ባልተጠበቀ መልኩ በውድድሩ የወረደ አቋም ስታሳይ በነበረቸው ሞሮኮ 4-1 ተሸንፋለች፡፡ የአትላስ አንበሶቹን 4 ግቦች መካከል አብደልጋኒ ሞአዊ ሁለት ሲያስቆጥር፣ መሃመድ አዚዝ እና አብደልዲም ካሃርዶፍ አስቆጥረዋል፡፡ የአማቩቢዎቹን ብቸኛ ግብ ሂግማን ናጎሚራኪዛ ከመረብ አዋህዷል፡፡ ውጤቱን ለሩዋንዳ የከፋ ቢሆንም ምድቡን በ1ኝነት ከማጠናቀቅ አላገዳትም፡፡

ከሁለቱ ሃገራት በተጨማሪ በኢትዮጵያ ምድብ የምትገኘው ዲ.ሪ. ኮንጎ እና በምድበ ብ4 የምትገኘው ዛምቢያ ከወዲሁ ወደ ሩብ ፍፃሜው መግባታቸውን ያረጋገጡ ቡድኖች ናቸው፡፡

12493921_1031264756934210_3808791868625162536_o

ያጋሩ