የክቡር ይድነቃቸው መታሰቢያ ውድድር እየተካሄደ ይገኛል

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር የሚያዘጋጀው 14ኛው የክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ መታሰቢያ ከ15 ዓመት በታች ዓመታዊ የታዳጊዎች ውድድር በአራት ምድብ ተከፍሎ ጀሞ በሚገኘው ዶንቦስኮ ሜዳ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በርካታ ታዲጊዎች በማሳተፍ ከክለብ አንስቶ እስከ ብሔራዊ ቡድን መጫወት የቻሉ ስመጥር ተጫዋቾችን ማፍራት የቻለው ውድድሩ ዘንድሮም ለ14ኛ ጊዜ እየተካሄደ ይገኛል። ከሐምሌ 24– ነሐሴ 7 ድረስ 68 ቡድኖች መካከል የማጣርያ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ሲካሄድ ሰንብቶ በመጨረሻም 16 ቡድኖች በመለየት በአራት ምድብ የተከፈለ ውድድር ከነሐሴ 13 ጀምሮ እያካሄደ ይገኛል። እስከ ነሐሴ 25 ድረስ የሚቀጥልም ይሆናል።

የምድብ ድልድል

ምድብ አንድ፡ ቤተሰብ፣ ሳሪስ አዲስ ሰፈር፣ ታቦት ማደሪያ፣ አብዲ ቦሮ

ምድብ ሁለት፡ ጨው በረንዳ፣ አንለያይም፣ ኤንፓ፣ ኮልፌ ፕሮጀክት

ምድብ ሦስት፡ አሰላ ፍሬ፣ ጫካ ሜዳ፣ ፉትቦል ላይፍ ፣ ጫጫ

ምድብ አራት፡ መካኒሳ፣ አዲስ ከተማ፣ ተስፋ ለኢትዮጵያ ፣ አዳማ ብሩህ ተስፋ

የመጀመርያ ቀን ውጤቶች

ቤተሰብ 1-1 ታቦት ማደሪያ
ሳሪስ አዲስ ሰፈር 1-3 አብዲ ቦሩ
ጨው በረንዳ 3-4 ኤንፓ
አንለያይም 2-2 ኮልፌ ፕሮጀክት

የሁለተኛ ቀን ውጤቶች

አሰላ ፍሬ 1-0 ፉትቦል ላይፍ
ጫካ ሜዳ 0-2 ጫጫ
መካኒሳ 1-0 ተስፋ ለኢትዮጵያ
አዲስ ከተማ 0-5 አዳማ ብሩህ ተስፋ

የሦስተኛ ቀን ውጤቶች

ቤተሰብ 2-1 ሳሪስ አዲስ ሰፈር
ታቦት ማደሪያ 0-2 አብዲ ቦሩ
ጨው በረንዳ 3-2 አንለያይም
ኤንፓ 2-0 ኮልፌ ፕሮጀክት

የአራተኛ ቀን ጨዋታዎች መርሐ ግብር

ሐሙስ ነሐሴ 16 ቀን 2011

02:30 | አሰላ ፍሬ ከ ጫካ ሜዳ
03:30 | ፉትቦል ከ ጫጫ
04:30 | መካኒሳ ከ አዲስ ከተማ
05:30 | ተስፋ ለኢትዮጵያ ከ አዳማ ብሩህ ተስፋ

* እጅግ አስገራሚ የሜዳ ላይ ፉክክክር በተመለከትነበት በዚህ የታዳጊዎች ውድድር የቀድሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የኃላ ደጀን በመሆን ተጫዋች እና በአሁኑ ወቅት የቅዱስ ጊዮርጊስ ጊዜያዊ አሰልጣኝ በመሆን እያገለገለ የሚገኘው የአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ ልጅ ነብዩ ዘሪሁን በአጥቂ ስፍራ ለታቦት ማደርያ እየተጫወተ ሲገኝ በአዳማ ከተማ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና በየመን እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ስኬታማ ዓመታትን ያሳለፈው የብርሃኑ ቃሲም ልጅ ሀሮን ብርሃኑ በተከላካይነት በአዳማ ብሩህ ተስፋ እየተጫወተ ይገኛል።

* በውድድሩ ላይ ከሚሳተፉ 16 ቡድኖች መካከል ጫጫ (ከደብረ ብርሃን) ፣ አሰላ ፍሬ(ከአሰላ) እና አዳማ ብሩህ ተስፋ (ከአዳማ) ረጅም ርቀት አቋርጠው በታዳጊዎች ውድድር ለመሳተፍ የወሰዱት ተነሳሽነት የሚያስመሰግናቸው ተግባር ነው።

* ያለፉትን 14 ዓመታት በውድድሩ ላይ ለሚሳተፉት ቡድኖች ወጪ እና በሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ተጫዋቾቹ ጉዳት ቢደርስባቸው አስፈላጊውን ህክምና እንዲያገኙ ድጋፍ በማድረግ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብነት ገብረ መስቀል ሙሉ ወጪውን በመሸፈን ያደረጉት ተግባርም የሚበረታታ ነው።

* የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ የፊታችን ቅዳሜ የሚጠናቀቅ ሲሆን ከየምድባቸው አንደኛ በመሆን የሚያጠናቅቁ አራት ቡድኖች በቀጥታ ወደ ግማሽ ፍፃሜው የሚያመሩ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡