የኢትዮጵያ እና ካሜሩን ሴት ብሔራዊ ቡድኖች የሚያደርጉት ጨዋታ በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ሽፋን እንደሚያገኝ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።
በ2020 የቶኪዮ ኦሊምፒክ የሴቶች እግርኳስ የአፍሪካ ዞን ሁለተኛ ዙር ማጣርያ አካል የሆነው የሁለቱ ሀገራት የመጀመርያ ጨዋታ በመጪው ሰኞ ሰኔ 20 ቀን 2011 ባህር ዳር ላይ የሚከናወን ሲሆን ጨዋታውም በዋልታ ቴሌቪዥን እንደሚተላለፍ ተገልጿል።
ሉሲዎቹ ባሳለፍነው ቅዳሜ ወደ ኬንያ በማምራት የወዳጅነት ጨዋታ አድርገው ከተመለሱ በኋላ ዝግጅታቸውን በባህር ዳር ሲቀጥሉ ተጋጣሚያቸው ካሜሩንም በተመሳሳይ ወደ ከተማዋ አምርተው ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ።
ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር በተያያዘ የሁለቱ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኞች እሁድ ባህር ዳር በሚገኘው ዊን ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።
© ሶከር ኢትዮጵያ
በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡