ቻምፒየንስ ሊግ| የመቐለ ጨዋታ በሁለት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በቀጥታ ይተላለፋል

በመጪው እሁድ በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ መቐለ 70 እንደርታ ከካኖ ስፖርት አካዳሚ የሚያደርጉትን ጨዋታ የትግራይ መገናኛ ብዙሀን (ኤመሐት) እና ድምፂ ወያነ ትግራይ ቀጥታ የቴሌቪዥን ሽፋን ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት እንዳጠናቀቁ ገልፀዋል።

ባለፈው የውድድር ዓመት የመቐለ የሜዳ ላይ ጨዋታዎች የቀጥታ ሽፋን የሰጠው ትግራይ ቴሌቭዥን ከአንድ ዓመት ገደማ በኋላ በድጋሚ የክለቡን ጨዋታ በቀጥታ የሚያስተላልፍ ሲሆን በቅርቡ የቴሌቭዥን ስርጭት የጀመረው ድምፂ ወያነ ትግራይ በአንፃሩ የመጀመርያ የቀጥታ ስርጭቱን የሚያደርግ ይሆናል።

በመጀመርያው ዙር ወደ ማላቦ አቅንተው በጠባብ ውጤት ተሸንፈው የእሁዱን ጨዋታ በመጠባበቅ የሚገኙት መቐለዎችም ለጨዋታው በሁሉም ረገድ ለየት ያለ ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ እንደሚገኙ መመልከት ችለናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡