የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔውን መስከረም ወር ላይ ያደርጋል

(ፌዴሬሽኑ አሁን ጉባዔውን በአንድ ሳምንት ገፍቶ ወደ ጥቅምት 1 አሸጋግሯል።)

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን 11ኛው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔኤ በሚቀጥለው ዓመት መስከረም ወር ላይ ይካሄዳል።

2010 በሰመራ በተካሄደው ምርጫ በአቶ ኢሳይያስ ጂራ ለሚመራው የፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የመጀመርያ የሆነው ይህ ጠቅላላ ጉባዔ 2012 መስከረም 24 ቀን አዲስ አበባ ላይ እንደሚካሄድ ታውቋል።

የእግርኳሱ መሠረታዊ ውሳኔዎች ይተላለፉበታል ተብሎ የሚጠበቀው እና ውዝግብ በማያጣው ጉባዔው ላይ በአጀንዳነት የተያዙ እና ሁሌም የሚነሱት እንደ ሒሳብ ሪፖርት፣ የስራ አፈፃፀም ሪፖርት እና የኦዲት ሪፖርት ማዳመጥ፣ በተጓደሉ አባላት ምትክ መምረጥ፣ የተሻሻለ የመተዳደርያ ደንብ ማፅደቅ እና የመሳሰሉት የሚገኙበት ሲሆን የፌዴሬሽኑ መለያ (ሎጎ) ማሻሻልም በአጀንዳነት ተይዟል።

በአንፃሩ የአዲስ አበባ ክለቦች ከአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ባስጠኑት የሊግ አደረጃጀት ለውጥ ዙርያ እንዲሁም የተጫዋቾች የደሞዝ የክፍያ መጠን ከ50 ሺህ ብር በላይ እንዳይበልጥ የተወሰነው ውሳኔ የጠቅላላ ጉባዔው አጀንዳ ሆኖ አለመቅረቡ ምን አልባት ቀዳሚ የውዝግብ ርዕስ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ