“ከቅዱሰ ጊዮርጊስ ጋር ለመስራት ውል ገብቼ ነበር” አሰልጣኝ ውበቱ አባተ


አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለማምራት የውል ስምምነት ፈርመው እንደነበርና ውላቸው ተቋርጦ ወደ ሰበታ ማምራታቸውን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡

ከፋሲል ከተማ ጋር በቅርቡ በግል ጉዳይ ምክንያት ከተለያዩ በኃላ በአዲስ አበባ የሚገኝ አልያም በቅርበት የሚገኘረ ክለብ የመስራት ፍለመጎት ያሳዩት አሰልጣኝ የሆነው ውበቱ አባተ ዛሬ የሰበታ ከተማ አሰልጣኝ መሆናቸው ይፋ ከተደረገበት ጋዜጣዊ መግለጫ በኋላ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ተስማምተው ስለለያዩበት መንገድ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። “ቅዱስ ጊዮርጊስ ትልቅ ክለብ ነው። እኔም የነሱን ፍላጎት ተረድቼ አብሬ ለመስራት ለሦስት አመት ውል ገብቼ ነበር” የሚሉት አሰልጣኙ ከሌሎች ክለቦች የመጣላቸውን የቅጥር ጥያቄ ውድቅ አድርገው ወደ ፈረሰኞቹ ቤት በር ላይ ደርሰው ስለመመለሳቸው ገልፀዋል።

 ” እኔ እስከ ማውቀው የጊዮርጊስ አሰልጣኝ ለመሆን ተስማምቼ ወደ ስራም እየገባው ነበር። አንዳንድ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ እንዲመጡ ያደረኩ ሲሆን በእጥልጥል የቀሩም ነበሩ። እኔን አምነው ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊገቡ ከኔ ጋር ተስማምተው የነበሩ ተጫዋቾችን ጠብቁኝ ብዬ ሳላስፈፅም በመቅረቴ ይቅርታን እጠይቃለሁ።” ብለዋል።

አሰልጣኙ በስተመጨረሻም “ለኔ ጥሩ ነገር የነበራቸውን ሰበታን ምርጫዬ አድርጊያለው ይላል፡፡ ከአዛም ጨዋታ አራት ቀን ቀደም ብሎ የሰበታ አመራሮች ባህር ዳር ድረስ መጥተው አሰልጣኝ ሁንልን ብለው አናግረውኝ ነበር። እኔ ከጊዮርጊስ ጋር ስለተስማማሁ ለመቀጠል ያሰብኩ ቢሆንም ጊዮርጊሶች ውል እናቋርጥ ብለው በመምጣታቸው የተነሳ ውሌን ቀድጄ ሰበታን ምርጫዬ አድርጊያለሁ።” ሲሉ አስተያየታቸውን አጠቃለዋል።

*ውበቱ አባተ የሰበታ ከተማ አሰልጣኝ ሆነው የተሾሙበትን ጋዜጣዊ መግለጫ ከቆይታ በኋላ ይዘን እንቀርባለን።


© ሶከር ኢትዮጵያ