የፕሪምየር ሊግ ባለ ድሉ አሰልጣኝ የመልቀቂያ ደብዳቤ አስገቡ

ላለፉት ሁለት ዓመታት ከጅማ አባ ጅፋር እና መቐለ 70 እንደርታ ጋር የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ያነሱት አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ለክለቡ የመልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸው ታውቋል።

ሶከር ኢትዮጵያ ከታማኝ ምንጮች እንዳገኘችው መረጃ አሰልጣኙ ባለፉት ቀናት ለክለቡ የልቀቁኝ ጥያዌ ማቅረባቸው ሲታወቅ የጥያቄው ምክንያትም አሰልጣኙ ከአንዳንድ ደጋፊዎች በመጣ ምላሽ ደስተኛ ባለመሆናቸው ነው ተብሏል።

ባለፈው ዓመትም በተመሳሳይ ጅማ አባጅፋርን የሊጉን ዋንጫ እንዲያነሳ ባስቻሉበት ማግስት ከቡድኑ ጋር የተለያዩት አሰልጣኙ ጥያቄያቸው አዎንታዊ ምላሽ የሚያገኝ ከሆነ በቅርብ ወራት ውስጥ ከውበቱ አባተ ቀጥለው በገዛ ፍቃዳቸው ቡድናቸውን የለቀቁ ሁለተኛ የሊጉ አሰልጣኝ ይሆናሉ።


© ሶከር ኢትዮጵያ