ኳታር 2022 | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ አመሻሽ ወደ ሌሶቶ ያቀናል

በ2022 ዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታውን ከሌሶቶ ጋር ያለ ጎል በአቻ ውጤት የተለያየው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለመልሱ ጨዋታ ዛሬ አመሻሽ ላይ ወደ ሌሶቶ ያቀናል።

እሁድ ጳጉሜ 3 የመልሱን ጨዋታ የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 20 ተጫዋቾችን ጨምሮ በጥቅሉ 28 የልዑካን ቡድን በመያዝ የሚያቀና ሲሆን በጉዳት ምክንያት ግብጠባቂው ምንተስኖት አሎ እና አማኑኤል ዮሐንስ ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር አብረው የማይጓዙ ተጫዋቾች ናቸው።

በዚህም መሠረት ወደ ሌሶቶ የሚያቀኑ ተጫዋቾች ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው፡-

ግብ ጠባቂዎች (2)፡ ጀማል ጣሰው፣ ለዓለም ብርሀኑ

ተከላካዮች (6) ፡ አህመድ ረሺድ፣ አስቻለው ታመነ፣ ያሬድ ባዬ፣ አንተነህ ተስፋዬ፣ ረመዳን የሱፍ፣ ደስታ ደሙ፣

አማካዮች (7): ጋቶች ፓኖም፣ ሽመልስ በቀለ፣ ቢንያም በላይ፣ ከነዓን ማርክነህ፣ ዮናስ በርታ፣ ሀይደር ሸረፋ፣ ፉአድ ፈረጃ

አጥቂዎች (5)፡ ሙጂብ ቃሲም፣ አማኑኤል ገ/ሚካኤል፣ ዑመድ ኡኩሪ፣ መስፍን ታፈሰ፣ አዲስ ግደይ

* የብሔራዊ ቡድን የዛሬው ጉዞ ምናልባት ሙሉ ለሙሉ ካልተጠናቀቀ ነገ ሊጓዙ እንደሚችሉ ሰምተናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ