በዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ነገ 10:00 ላይ ሌሶቶን ያስተናግዳል። በጨዋታው ዙርያ ያሉ ጠቃሚ መረጃዎችን እንዲህ አጠናቅረናል።
– ዋሊያዎቹ የመጨረሻ ልምምዳቸውን በባህር ዳር ኢንተርናሽናል ስታድየም ዛሬ ረፋድ 4 ሰዓት በማከናወን ለሌሶቶው ጨዋታ ሙሉ ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል።
– ሦስቱ ጥሪ የተደረገላቸው በውጪ የሚጫወቱ ትውልደ ኢትዮጵያውያን (አሚን አስካር፣ ዳንኤል ተሰማ እና ካሊድ ሙሉጌታ ለሌሶቶው ጨዋታ መድረስ አለመቻላቸውን አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ የገለፁ ሲሆን ተጫዋቹም ከዚህ በፊት ለኢትዮጵያ ቤሄራዊ ቡድን ተጫውተው የማያውቁ በመሆናቸው የፊፋን ፍቃድ ማግኘት እንዳልቻሉ፤ በዚህም ምክንያት ለነገው ጨዋታ እንዳልረሱ ተገልጿል ።
– የምስር ኤል ማቃሳው አማካይ ሽመልስ በቀለ ቡድኑን በአምበልነት እየመራ ወደ ሜዳ ይገባል። ሽመልስ የዋናው ብሔራዊ ቡድንን የመጨረሻ የነጥብ ጨዋታ (ጋና 0-2 ኢትዮጵያ) በአምበልነት መምራቱ ይታወሳል።
– የሀራስ ኤል ሁዳዱ አማካይ ጋቶች ፓኖም ዘግይቶ (ትናንት) ብሔራዊ ቡድኑን የተቀላቀለ ሲሆን ዛሬ ቀለል ያለ ልምምድ መስራት ችሏል። ምናልባትም ጋቶች ፓኖም ዘግይቶ ከመቀላቀሉ አንፃር ከቡድኑ ጋር ላይዋሀድ ይችላል የሚል ስጋትም አለ።
– የባህር ዳር ኢንተርናሽናል ስታዲየም ቴኬት ሽያጭ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ስታድየም አካባቢ ሽያጭ እንሚጀምር ተገልጿል። 6:00 ሰዓት ላይ የስታዲየም በር ለደጋፊዎች ክፍት እንደሚሆን የም ታውቋል።
– 74 ሺህ ትኬት እንደተዘጋጀ የተነገረለት የነገው ጨዋታ የመግቢያ ዋጋ ይፋ ሲደረግ 1ኛ ደረጃ 200 ብር፣ 2ኛ ደረጃ 100 ብር፣ 3ኛ ደረጃ 50 ብር እንዲሁም 4ኛ ደረጃ 30 ብር ተተምኖላቸዋል።
– ቀጥታው በአማራ ቴሌቪዥን የቀጥታ ሽፋን እንደሚሰጠው ከአማራ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት ያገኘነው መረጃ ይጠቁማሉ።
© ሶከር ኢትዮጵያ