ኢትዮጵያን ፕሮፌሽናል ፉትቦለርስ አሶሴሽን ስብሰባ ጠራ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ነሐሴ 3 እና ነሐሴ 25 በጠራው ስብሰባ ያሳለፈውን የተጫዋቾች የደሞዝ ጣርያ ውሳኔ በተመለከተ ኢትዮጵያን ፉትቦለርስ አሶሴሽን ስብሰባ ጠርቷል።

ማኅበሩ ለሚድያዎች በላከው መረጃ መሠረት ፌዴሬሽኑ የወሰነውን ውሳኔ በመቃወም ያወጣቸውን መግለጫዎች ፌዴሬሽኑ ችላ በማለቱ አባላቶቹን መሰብሰብ እንዳስፈለገ ገልጿል።

በቅርቡ የተመሰረተው ማኅበሩ በመጪው እሁድ ጳጉሜ 3 ቀን 2011 በፕሪምየር ሊጉ፣ ከፍተኛ ሊጉ እና አንደኛ ሊግ የሚገኙ ክለብ አምበሎች ወይም ተወካዮች በስብሰባ እንዲገኙ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ከተጠቀሱት በተጨማሪ ማንኛውም ተጫዋች የመገኘት መብት እንዳለው ገልጿል።

ማኅበሩ በተጨማሪም በፌዴሬሽኑ ውሳኔዎች ዙርያ ያለውን ወቅታዊ አቋም በሚከተለው መልኩ አሳውቋል:-


© ሶከር ኢትዮጵያ