የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 4ኛ ሳምንት ጨዋታዎች

 

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 4ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በመጪው ቅዳሜ እና እሁድ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይቀጥላል፡፡ 9 እና 7 ነጥብ ይዘው በምድብ ሀ ሰንጠረዥ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃ ላ የተቀመጡት ወልድያ እና ወልዋሎ መልካ ቆሌ ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ከፍ ያለ ግምት ከሚሰጣቸው መርሃ ግብሮች አንዱ ነው፡፡ ወሎ ኮምቦልቻ ከ አአ ፖሊስም ተጠባቂ ጨዋታ ነው፡፡

A week4 HL

ከምድብ ለ መሪው አአ ከተማ በጥሩ አቋም ላይ የማይገኘው ፌዴራል ፖሊስን አበበ ቢቂላ ላይ ይገጥማል፡፡ ደቡብ ፖሊስ ከ ጅማ አባቡና ከምድቡ በዚህ ሳምንት የሚጠበቅ ሌላው ጨዋታ ነው፡፡

በዚህ ምድብ ነቀምት ከተማ ከ ናሽናል ሴሜንት የሚያደርገው ጨዋታ በፀጥታ ጉዳዮች ምክንያት ጨዋታው በነቀምት ይደረግ አይደረግ እስሁን ውሳኔ አልተሰጠም፡፡ ነቀምት የፀጥታ ሁኔታውን እስከ ሀሙስ ማረጋገጥ ካልቻለና ሀላፊነቱን ወስዶ ጨዋታው ነቀምት እንዲደረግ ካላሳወቀ ፌዴሬሽኑ ጨዋታው በአዲስ አበባ እንደሚያከናውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ነቀምት የ2ኛ ሳምንት ጨዋታውን ከጂንካ ከተማ ጋር በአዲስ አበባ ስታድየም ማድረጉ ይታወሳል፡፡

hl new

 

የምድቦቹን የደረጃ ሰንጠረዥ ለማወቅ ይህንን ሊንክ ይጫኑ ፡- Soccerethiopia.net

ያጋሩ