ኳታር 2022| “ከኢትዮጵያ ጋር ያስመዘገብናቸው ያለፉ ውጤቶች አያስጨንቁንም” ታቦ ሴኖንግ


ለኳታር 2022 የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ የኢትዮጵያ ቤሔራዊ ቡድንን ለመግጠም ባህር ዳር የገቡት ሌሶቶዎች ዛሬ 10:00 ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ጨዋታውን አስመልክቶ በተዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫም የዛሬ ሳምንት ቡድኑን በአሰልጣኝነት የተረከቡት ታቦ ሴኖንግ አስተያታቸውን ሰጥተዋል።

ስለ ዝግጅታቸው

ባህር ዳር ከገባን ጀምሮ ልምምድ እየሰራን ነው። ኢትዮጵያ ጥሩ ቡድን እንዳላት እናውቃለን፤ ጨዎታው ከባድ እንደሚሆንም እናምናለን። ተጋጣሚያችንን አክብረን ጨዋታውን በትኩረት እና በጥንቃቄ እንጫወታለን።

ስለ ቡድኑ ቅንጅት

የሌሶቶን የአጨዋወት ባህል አውቀዋለሁ። ለማስልጠን ዋናው ምክኒያቴም እሱ ነው። እውነት ነው ጊዜው አጭር መሆኑ ለኔም ሆነ ለተጫዋቾቸ ከባድ ነው። እንዴት እንደምሄድ ለመረዳት ጊዜ ያስፈልጋቸዋል፤ ለኔም ጊዜ ያስፈልገኛል። በሂደት የሚታይ ነገር ነው።

ብሔራዊ ቡድናችሁ ከኢትዮጵያ በሜዳችሁም ከሜዳ ውጭም ጋር ጥሩ የውጤት ታሪክ የለውም…

እግርኳስ ስላለፈው ነገር ሳይሆን ስላለንበት እና ስለ ወደፊት የምናስበው ነው። ያለፈው ወጤት አያስጨንቅም። የኢትዮጵያን ያለፉትን 5 ጨዋታዎች አይተናል። 12 ግቦች ተቆጥረውባት 1 ግብ ነው ያስቆጠረችው። ነገር ግን ከትልልቅ ብሔራዊ ቡድኖች ጋር እንደመጫወቷ ኢትዮጵያ ጥሩ ቡድን አይደለችም ማለት አይቻልም። ምክኒያቱም እያንዳንዱ ቀን ለመቀየር የራሱ የሆነ እድል አለው የ። በየቀኑ የተሻለ ነገር መስራት ይቻላል። እኛ ካለፈው ነገር ተምረን የተሻለ ለመስራት ተዘጋጅተናል ።


© ሶከር ኢትዮጵያ