የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ፉትቦለርስ አሶሴሽን ክስ ሊመሰርት ነው

የኢትዮጵያን ፕሮፌሽናል ፉትቦለርስ አሶሴሽን በአሁኑ ሰዓት በዋቢ ሸበሌ ሆቴል እያደረገ ባለው ስብሰባ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ላይ ክስ ሊመሰርት እንደሆነ ገልጿል።

ከደቂቃዎች በፊት በጀመረው በዚህ ስብሰባ የአሶሴሽኑ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ግርማ ፣ የአሶሴሽኑ ፀሃፊ አቶ ሳምሶን እና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ተገኝተዋል። በቦታው ከተገኙ የየክለቦች አምበሎች ጋር እየተደረገ ባለው ውይይትም አሶሴሽኑ ከቀናቶች በፊት የተወሰነው የተጨዋቾች ደመወዝ ገደብን አስመልክቶ የመጨረሻ ውሳኔ አሳልፏል። በውሳኔውም ማህበሩ ለፌደሬሽኑ ያስገባቸው ደብዳቤዎች እስከ መጪው ሐሙስ ድረስ ምላሽ ካልሰጠ ወደ ፍርድ ቤት ሊያመሩ እንደሆነ ገልፀዋል።

የስብሰባውን ዝርዝር ዘገባ ከቆይታ በኋላ ይዘን እንመለሳለን።


© ሶከር ኢትዮጵያ