በቻን ማጣርያ ሩዋንዳን የሚገጥሙት ዋልያዎቹ መስከረም ሁለት በመቐለ ዝግጅታቸው ይጀምራሉ።
የሃገር ውስጥ ሊግ ተጫዎቾች ብቻ ለሚሳተፉበት የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) ማጣርያ እያደረጉ የሚገኙት ዋልያዎቹ መስከረም 12 በትግራይ ስታዲየም ላላቸው የሁለተኛ ዙር ጨዋታ ዝግጅታቸውን ነገ መስከረም ሁለት በመቐለ ይጀምራሉ። በስብስባቸው ላይም የተወሰነ ለውጥ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ባለፈው ወር የአፍሪካ ውድድሮች ለማዘጋጀት ፍቃድ ያገኘው የትግራይ ስታዲየም ሁለት ደረጃቸው የጠበቁ የልምምድ ሜዳዎች የያዘ ሲሆን በዚህ ሰዓት ወልዋሎ እና መቐለ 70 እንደርታ በሜዳው የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸው በማድረግ ይገኛሉ።
በመጀመርያው ማጣርያ ጅቡቲን ያሸነፈው ብሄራዊ ቡድኑ መስከረም 12 ሩዋንዳን የሚገጥም ሲሆን መቐለ ከተማም በታሪኳ ለመጀመርያ ጊዜ የብሔራዊ ቡድን የምታስተናግድ ይሆናል።
© ሶከር ኢትዮጵያ