ድሬዳዋ ከተማ ያሬድ ሀሰንን የክለቡ ስምንተኛ ፈራሚ በማድረግ ሲያስፈርም አምስት ወጣቶችን አሳድጓል፡፡
የቀድሞው የወልድያ ከተማ የግራ መስመር ተከላካይ ያሬድ ሀሰን በ2011 ወደ መቐለ 70 እንደርታ አምርቶ ከክለቡ ጋር ግን የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ካነሳ በኃላ ማረፊያውን የምስራቁ ክለብ በማድረግ በአንድ ዓመት ውል አምርቷል፡፡
ድሬዳዋ ከተማ እስከ አሁን ስምንት አዳዲስ ተጫዋቾችን ከማስፈረሙ ባለፈ ከወጣት የክለቡ ቡድን አምስት ተጫዋቾችን አሳድጓል፡፡ አብዩ ካሳዬ (ግብ ጠባቂ)፣ ዱጉምሳ አብደላ (ተከላካይ)፣ ወንደሰን ደረጀ (አማካይ)፣ አቤል አሰበ (አማካይ) ያሬድ አበርጋ (አጥቂ) ወደ ዋናው ቡድን ያደጉ ተጫዋቾች ናቸው፡፡
በተያያዘ ዜና ክለቡ የአሰልጣኝ ስምዖን ዓባይ ሦስተኛ ረዳት አሰልጣኝ በማድረግ ደግሞ አቤል አሰበን ከ20 ዓመት ቡድኑ ወደ ዋናው ከፍ አድርጓል፡፡
የፊታችን ቅዳሜ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን በመቐለ የሚጀምረው ድሬዳዋ ለሀገር ውስጥ እና የውጪ ተጫዋቾችን የሙከራ ዕድልን በስፋት እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡.
© ሶከር ኢትዮጵያ